ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ድሬዳዋ – የአምስት ሳምንት እውነታዎች

➖  የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያ በተመረጡ አምስት ከተሞች እንዲካሄድ ተደርጎ ከ17ኛ ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት አራተኛዋ የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በድሬዳዋ ከተማ ከዕረቡ መጋቢት – ሚያዚያ 20 /2013 ዓ.ም ተከናውኗል።
➖የድሬዳዋ ስቴድየም የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከ17ኛ ሳምንት እሰከ 21ኛው ሳምንት 30 ጨዋታዎች ተካሄደዋል።
➖ ለመጀመሪያ ጊዜም የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በምሽት ተካሄዷል።
➖ለመጀመሪያ ጊዜ የድሬዳዋ ስታዲየም ያስተናገደው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ ሲሆን ጨዋታው በ10: 00 ሰአት ተካሄዶ ጨዋታው ያለ ጎል ባዶ ለባዶ ተጠናቋል።
➖ የመጀመሪያው የምሽት ጨዋታ በ1:00 ሰአት የተካሄደው ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በሃዋሳ ከተማ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
➖ በድሬዳዋ ስታዲየም የተካሄዱት ሁሉም ጨዋታዎች በ10:00 ሰአት እና ምሽት 1:00 ሰአት ላይ በሱፐር ስፓርት ሽፋን አግኝተዋል።
➖አንጋፋውና የሶስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ያስተናገደው ታሪካዊው የድሬደዋ ኢንተርናሽናል ስታዲዮም ከጥር እስከ ሚያዝያ 96 ጨዋታዎች አስተናግል ። ይህም
66 ሱፐር ሊግ ጨዋታዎች እና 30 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተካሄደውበታል። በአንፃሩ የድሬ ሜዳ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ   ለማጫወት ጨዋታዎች አስቸግሮም ታይቷል። ረጅም አመት ያገለገለው የድሬ ሜዳ ተተኪ እንደሚሻም በቤትኪንግ ውድድር ተስተውሏል።
➖የቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር በድሬዳዋ ስታዲየም በ30 ጨዋታዎች 60 ጎሎች ተቆጥረዋል።
➖በድሬደዋ ከቤትኪንግ ውድድር ጎን ለጎን ኮቪድ እና የቡድኖች የምርመራ ውጤት አነጋጋሪነቱን ሆኖ ተጠናቋል። በተለይም ደግሞ የቡድኖች ውጤት ከሁለቱ ተቋማት የተለያዩ ሆነ ምላሽ ነበር ። ክለቦች በድሬዳዋ የምርመራ ውጤታቸው ኮቪድ አለባችሁ ተብለው በአለማያ ዮኒቨርስቲ ነፃ ናችሁ የሚባሉ ተደጋጋሚ ክስተቶችን በአምስት ሳምንት ቆይታ ተስተናግደዋል።
➖ በድሬደዋ የተካሄደው የ2013 ዓ.ም የቤትኪንግ ውድድር የሸገር ደርቢ አስተናግዶ ነበር። ሚያዚያ 10 ምሽት በተካሄደው ተጠባቂዉ የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 ተሸንፏል።
➖ በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው የቤትኪንግ ውድድር በርካታ ወጣት ተጨዋቾች የታዮበት ነበር ማለት ይቻላል። በአንፃሩ በቤትኪንግ ጎልተው ሲታዮ የነበሩ ተጨዋቾች በመጠኑ ቀንሰው ታይተዋል።
➖ የከተማው ክለብ ድሬደዋ ከተማ በሜዳው ያደረጋቸው ጨዋታውች ከአምስቱ ሁለት አሸነፎ ፣ሁለት አቻ ወጥቶ አንዱን ብቻ ተሸንፏል። በአንፃሩ በሊጉ ካሉ ክለቦች በተደጋጋሚ ሻምዮና የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የድሬዳዋ ቆይታው እጅጉን ደካማ ነበር። የድሬዳዋ ቆይታው የተሸለ ከነበሩ ክለቦች ሃዋሳ ከተማ ይጠቀሳል። ከአምስት ጨዋታ ሶስት ማሸነፍ ችሏል። የዘንድሮው የቤትኪንግ ሻምፒዮናነቱን ለማንሳት የተቃረቡት ዓፄዎቹ ከአምስት ጨዋታ ሶስቱን አሸንፈው ሁለቱን አቻ በመውጣት የሚፈልጉትን ውጤት ከድሬዳዋ ይዘው ወጥተዋል።
➖በድሬደዋ የቤትኪንግ ቆይታ አስገራሚ ከነበረው የ19ኛው ሳምንት የምሽቱ ወላይታ ድቻ ከ ሃዋሳ ከተማ ጨዋታ አንድም ተቀያሪ ተጨዋች ሳይኖረው በ11 ተጨዋቾች ብቻ ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ገጥሞው ጨዋታን በ3 ለ 2 ተሸናፊነት አጠናቋል። ለችግሩ በዋነኝነት የኮቪድ ወረርሸኝ እና የተጨዋቾች ተደራራቢ ጨዋታ ለጉዳት በቀላሉ መጋለጥ ዋነኞቹ ሲሆኑ በወላይታ ድቻ በኩል ሁለቱን ግብ ጠባቂዎች በአጥቂ ቦታ ላይ አሰልፈው ተጫውተዋል