የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያት በተለያዪ ከተሞች አየተዘዋወሩ እንዲደረጉ በሚል በተመረጡ አምስት ከተሞች እየተካሄ ይገኛል።
የሊግ ካምፓኒው ከሳምንታት በፊት የ16ቱን የውድድሩን ሳምንታት ጨዋታዎች ግምገማ አድርገው እንደነበር ይታወሳል።በወቅቱ የሊግ ኮሚቴው የቦርድ ፕሬዝዳንት የ፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ ፉክክሩ በቀጣይ የሚካሄድባቸው ሀዋሳ እና ድሬዳዋ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ቀዳሚዎቹ አካባቢዎች መሆናቸውን ተናግረው ክለቦችን አስጠንቅቀውም እንደነበር ይታወቃል። በወቅቱ የቦርድ ፕሬዝዳንት የ፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ ውድድሩ በወረርሽኙ ምክንያት እንዳይቋረጥ ክለቦቻችን ትልቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበው ” ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ለሻይ እና ለሽርሽር ብለው ከሆቴል እንዳይወጡ መከልከል አለባቸው” በማለት ማሳሰባቸው ይታወሳል።
በአንፃሩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ17ኛው ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት የሊጉ ከጅማሮ ክለቦች የኮቪዲ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ እየተሰማ ነው። እንደ መረጃው ከሆነ አብዛኞቹ ክለቦች በኮቪድ የሚያዙ ከሆነ እና የኮቪድ ፕሮቶኮል የማያሟሉ ከሆነ የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የፎርፌ ውሳኔዎች እንደሚኖሩም መረጃዎች እየጠቆሙ ይገኛል።
በተያያዘ ዜናም የትላንቱ የድሬደዋ ስታዲየም የመክፈቻ ጨዋታ ሊመሩ የነበሩት የመሀል ዳኛ በኮቪድ በመያዛቸው ምክንያት ኢንተርናሽናል አርቢተር ሊዲያ ጨዋታውን መምራቷ ይታወቃል። በዛሬው የኮቪድ ዜና ደግሞ የአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ወላይታ ድቻ ለሁለተኛው ዙር ራሱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ላይ ሆኖ የጨዋታውን መጀመር በሚጠብቀበት ሰአት ሰባት የሚጠጉ ተጨዋቾች በኮቪድ መያዛቸው ተሰምቷል።
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ክለቦች በኮቪድ ጥንቃቄዎች ላይ ተጨዋቾቻቸውን ግንዛቤውን የበለጠ ማሳስብና ለችግሩ የጥንቃቄ መፍትሔ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሲገለፅ በዚህ ጉዳይ የሊግ ካምፓኒው ወሳኔ ለማስተላለፍ በአሁኑ ስብሰባ ላይ መሆኑም ተሰምቷል።