ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻው ምዕራፍ ነገ ሐዋሳ ላይ ይጀመራል! ➖ የተመልካች ቁጥር ?

የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያት በተለያዪ ከተሞች አየተዘዋወሩ እንዲደረጉ በሚል በተመረጡ አምስት ከተሞች ሲካሄድ ቆይቶ የፍፃሜ ምህራፍ ላይ ደርሷል።  የመጨረሻው የውድድሩ አዘጋጅ ከተማ ሀዋሳም  እንግዶቿን ለአንድ ወር ለማሰተናገድ ዝግጁ ሆናልች ። ተሳታፊ ክለቦች አብዛኞቹ ቡድኖችም ከቀናት በፊት ሐዋሳ የደረሱ ሲሆኑ ከክለባቸው ጋር በተከሰቱ ቅራኔዎች ምክንያት ተጠቃለው ሙሉ ለሙሉ ሆቴል ያልገቡ ተጨዋቾች እንዳሉም እየተሰማ ነው።
የውድድሩ የበላይ የሆነው በሊግ ካምፓኒው በኩል ደግሞ  የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሐዋሳ ለመቋጨት  እና  ዋንጫ  እንዲሁም የተለያዩ የመዝጊያ ዝግጅቶች ለማድረግ  እየተዘጋጀ  መሆኑ ተሰምቷል ።   በአንፃሩ የኮቪዲ ችግር የታሰበውን ያህል በቀላሉ ለማሳካትም እንቅፋት እንደሆነበት  ቢነገርም  የሊግ ካምፓኒው   ሃሳቡን ቅጥሎሷል።  እንደሚታወሰው የኮቪድ ፕሮቶኮል ክለቦች የማያሟሉ ከሆነ የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሊቋረጡ ይችላሉ ተብሎም ክለቦች ያለ ተቀያሪ ግብ ጠባቂዎችን አጥቂ ቦታ አሰልፍው ውድድሩ  አሁን ላይ  የመጨረሻው ምህራፍ ላይ ተደረሷል።
በተያያዘ መረጃ ከ22ኛው እስከ 26ኛው ሳምንት የሚካሄደው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻው  ምዕራፍ ያለ ተመልካች እንደሚሆን ምንጮች ጠቁመዋል።  በሊግ ካምፓኒው ኮሚቴዎች እና  የቦርድ አመራሮችት በኩል  የተመልካቾች   ቁጥር በተመለከተ ለ10 ተመልካቾች የሚለው ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ  ተቀባይነት  ማግኘት የቻለ አልሆነም።  ስለሆነም  አስራ አምስት ሺ ተመልካች የሚይዘው ዘመናዊ  የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያለተመልካች  ከ22ኛው እስከ 26ኛው ሳምንት  የሚደረግ  ይሆናል ።