ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ቀጣይ አስተናጋጅ ድሬዳዋ እንግዶቿን በድምቀት መቀበሏን ቀጥላለች !

የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያ በተመረጡ አምስት ከተሞች እየተካሄ ይገኛል። በቀጣይ ሳምንት ከ17ኛ ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት የምታስተናግደው አራተኛዋ የቤት ኪንግ  ፕሪምየር ሊግ አስተናጋጅ የድሬዳዋ ከተማ ትሆናለች ። ድሬዳዋ  የቤት ኪንግ  ፕሪምየር ሊግ  ለመጀመሪያ ጊዜም  በምሽት ጨዋታዎቹን ለማስተናገድ የስታድየም መብራቶች እና የስታዲየም እድሳቶችን በማድረግ አዘጋጇ ከተማ ዝግጅቷን አጠናቃለች ።   አሁን  ላይ ደግሞ ድሬ  እንግዶቿን በደማቅ አቀባበል እየተቀበለች ትገኛለች ።

ዛሬን ጨምሮ አብዛኞቹ የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦችም ድሬዳዋ የደረሱ ሲሆን በከተማው የስፖርት ቤተሰብ   ፣ በድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች እና በስፍራው በሚገኙ የየክለቦቹ ደጋፊዎች ጋር በመሆን የደረሱትን ቡድኖች በሞተር በማጀብ የእንኳን ደህና መጣችሁ ደማቅ አቀባበል እያደረጉ ይገኛሉ።  እንደሚታወቀው ውድድሩ በታሪካዊቷ የድሬዳዋ ስቴድየም የፊታችን እሁድ መጋቢት 26/2013 ይጀመራል ተብሎ ቢጠበቅም የአክሲዮን ማህበሩ ዛሬ ባሳወቀው ደብዳቤ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ለአፍሪካ ዋንጫ ከማለፍ ጋር በተያያዘ ለብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች ሽልማት በመታሰቡ ውድድሩ በማድረግ ከነበረበት ቀን ለሶስት ቀናት የተራዘመ ሲሆን መጋቢት 29/2013 ይጀመራል።