ዜናዎች

“የቅ/ጊዮርጊሱ ዘሪሁን ሸንገታ እሱ ለእኔ የአንደኛ ዙር ምርጥ አሰልጣኝ ነው” ➖ ጊልበርት ሰለቧ (የሱፐርስፖርት -ተንታኝ)

የቤትኪንግ ኢትዮዽያ ፕሪምየር ከ2013 ዓ.ም ወዲህ በዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት በአገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲታወቅ አምና ኬኒያዊያኑ ኮሜንታተሮች በርናልድ ኦቴዩ እና ጊልበርት ስለቧ ዘንድሮም ከዮጋንዳዊው ጋዜጠኛ አንድሪው ካቡራ ጋር በተመሳሳይ ኬኒያዊው ጊልበርት ሰለቧ በቀጥታ ሽፋኑ ሙያዊ ትንታኔዎች እየሰጠ ይገኛል።
አትዮ -ኪክ ከዚህ ቀደም እንደምናደርገው ኬኒያዊው ጊልበርት ሰለቧ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቻምፒዮና ማን ሊሆን ይችላል? በአንደኛ ዙር ውድድርን በተከሰቱ በርካታ የዳኝነት ችግሮች በመነሳት መፍትሄው VAR በሚሉት እና ፣ የዘንድሮ የቤትኪንግ ሻምፒዮና እና ኮከብ ግብ አስቆሪ ማን ይሆናል በሚለው እና የተለያዩ የሊጉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ኬኒያዊው ጊልበርት ሰለቧ ከኢትዮ ኪክ ጋር ቆይታ አድርጓል እንሆ እንላለን!
ኢትዮ ኪክ :– የዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የአንደኛ ዙር ውድድሮችን ጊልበርት ዕይታ እንዴት ይገመገማል ?
ጊልበርት:- አንደኛ ዙር በእኔ ዕይታ መሻሻል ያየሁባቸው ቦድኖች ነበሩ። ለምሳሌ ሀዋሳ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ እንዲሁም ጅማ አባጅፋር ቡድኖች ላይ በጨዋታ መሻሻል አሳይተዋል። ከጨዋታው ጎን ለጎን ደግሞ በአንደኛ ዙር ካየሁት እና ትኩረት መስጠት ያለበት ነገር ዳኞች ችግር ነው። በርካታ መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ያሉ ሲሆን የዳኞቹን ብቃት በቀጣይ ዙር መስተካከል አለበት።
ኢትዮ ኪክ :- በአንደኛ ዙር የዳኞች ስህተቶች ግልጽ ነበር ማለት ይቻላል ?
ጊልበርት:- አዎ ! በአንደኛው ዙር ረዳት ዳኞች በርካታ ስህተቶች ታይተዋል። ስህተቶች እየጨመሩ መጥተዋል።
ኢትዮ ኪክ :-የዳኝነት ችግሮችን ለመቅረፍ ምን ይደረግ ትላለህ ?
ጊልበርት-: የተለያዩ ዕውቀት ማሻሻል ኮርሶች ቢሰጡ እና የአካል ብቃት ፈተናዎች በተደጋጋሚ ቢኖር እላለሁ።
ኢትዮ ኪክ :- በአንደኛ ዙር ከነበረው በችግሩ በመነሳት ለሁለተኛው ዙር የቤትኪ ንግ ኢትዮጵያ ሊግ VAR መፍትሔ ይሆን ?
ጊልበርት:- አዎ በርግጥም የሚቻል ቢሆን ጥሩ አማራጭ ይሆን ነበር ።
ኢትዮ ኪክ :- ከዳኝነት ወደ አንደኛ ዙር የተጨዋቾች ብቃት እንሂድና ስለ ተጫዋቾቹ ግላዊ ችሎታስ በአንደኛ ዙር አድናቆት የሰጠሀቸው ተጨዋቾች ይኖራሉ ?
ጊልበርት:- በጣም እንጂ ..በጣም አድናቆት ከሰጠዋቸው ተጨዋቾች መሐል እንደነ እዮብ አለማየሁ፣ የአዲስ አበባ ከተማው ፍፁም ጥላሁን ፣ የአዋሳው ወንድማገኝ ኃይሉ ፣ የሀዲያ ሆሳዕናው ፍሬዘር ካሳ እና ሌሎች ወጣት ተሰጥኦዎ ያላቸውን ተጨዋቾች ማየት ተችሏል ።
ኢትዮ ኪክ :- የዘንድሮስ የጎል አስቆጣሪነት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ?
ጊልበርት:- በዘንድሮው የአንደኛ ዙር በርካታ ቡድኖች እስከ 4 ጎሎች የማስቆር አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ አይተናል። በርግጥ እሮግጠኛ መሆን አልችልም ጎሎቹ የተቆጠረበት በአጥቂዎቹ ጥሩ መሆን ወይስ የተከላካይ ተጨዋቾች ደካማ መሆን የሚለውን እርግጠኛ መሆን አልችልም። ሌላው ያየሁት ነገር አብዛኞቹ ጨዋታዎች ፈጣን እንቅስቃሴ መሆን ስህተቶ በተቀራረበ እና በቀላሉ መከሰት ምክንያት ሆኗል።
ኢትዮ ኪክ :- ባለፈው አመት በ29 ጎሎች አቡበከር ናስር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነበር፤ በዚህ አመት ኮከብ ግብ አግቢ ማን ይሆናል ትላለህ?
ጊልበርት:- አዎ ባለፈው አመት በ29 ጎሎች አቡበከር ነበር። በዘንድሮም የውድድር ዓመት አዲስ የጎል አስቆጣሪ እንደምናይ እርግጠኛ ነኝ። በዚህ ሲዝን አዲስ ከፍተኛ ግብ አግቢ ይኖራል። የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ኢስማኤል ኦሮ – አጎሮ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ።
ኢትዮ-ኪክ :- ስለዚህ የአንደኛ ዙር በ10 ጎሎች የጨረሰው ኢስማኤል ኦሮ – አጎሮ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ይጨርሳል ?
ጊልበርት:- አዎ ! ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ባለበት በመሪነቱ ከቀጠለ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ኢስማኤል ኦሮ – አጎሮ የዘንድሮ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ይሆናል ብዬ አምናለሁ
ኢትዮ-ኪክ :- የዘንድሮው የቤትኪንግ ሊግ ቻምፒየንስ ማን ሊሆን ይችላል ትላለህ?
ጊልበርት:-ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን እየሄደበት ባለው ሁኔታ የመሸነፍ ነገር ከሌለ በጣም ጥሩ ሂደት ላይ ነው ያሉት። ግን ደግሞ ሌሎቹም ጠንካራ ቡድኖች የቻምዮናነት ጉዞ ውስጥ አሉ፣ ለእኔ ፋሲል ከነማ በሩጫው ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል። በርግጥ ሁለተኛው ዙር የሂሳብ እና ማስላት ሂደት ነው።
ኢትዮ-ኪክ :- የአንደኛ ዙር ምርጥ አሰልጣኝ ላንተ ማን ነው ?
ጊልበርት:-የቅ/ጊዮርጊሱ ዘሪሁን ሸንገታ ከቀድሞ አሰልጣኝ ክራምፖቲች ከተረከበ በኋላ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ቡድኑን ጥሩ ደረጃ ላይ ነው። እሱ ለእኔ የአንደኛ ዙር ምርጥ አሰልጣኝ ነው።
ኢትዮ-ኪክ :- የሁለተኛው ዙር ውድድር በቅርብ ሳምንታት አዳማ ላይ ይቀጥል ፣ በቀጣይ ዙር እንዲሻሻል የምትለው ?
ጊልበርት:- በቀጣይ ዙር ዳኝነቱ እንዲሻሻል እመኛለሁ። ሌላው ግን የምመኘው ነገር ቢኖር ክለቦች ሙሉ አውቶብሳቸውን ታዳጊ ተጨዋቾችን ሞልተው ተተኪና ተስፋ ያላቸውን ታዳጊ ተጫዋቾቻቸው ዕድል ቢሰጡና ነፃ እግር ኳስን መጫወት ቢችሉ። ምክንያቱም በዚህ ሊግ ውስጥ በርካታ ትልቅ ደረጃ የሚደርሱ ታዳጊዎች አሉና።
ኢትዮ-ኪክ :- ስለነበረን ጊዜ ጊልበርት ሰለቧ አመሠግናለን !