ዜናዎች

– የሴካፋ አዘጋጅ ኢትዮጵያ ከሻምፒዮናው ውጪ ለመሆን ተቃርባለች! – የተሻለ ሁለተኛ ሆኖ ማለፉ ነገ ይታወቃል !

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 10 እስከ 25/2013 ዓ.ም ድረስ በዘጠኝ የሴካፋ አባል አገራት መካከል በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ውድድር የምድቡ ሃላፊዎች እየተወቁ ይገኛል። ወደ ቀጣይ ዙር ኃላፊ የሚሆነውን ለማወቅ አዘጋጇ ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ ባደረጉት የምድብ ” ለ” የዛሬ ጨዋታ በ1 ለ 1 በአቻ በመጠናቀቁ ተከትሎ ቡሩንዲ በ4 ነጥብ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች በመክፈቻው ጨዋታ ከኤርትራ አቻቸው ጋር በ3 ለ 3 አቻ ውጤት መጀመሩ ይታወሳል።በሦስት ምድብ ተከፍሎ ቀጣዮን ኃላፊ ለመለየት በተካሄደው የምድብ ውድድር  ኢትዮጵያ በምትገኝበት ከምድብ ” ለ’ ‘ የሚገኘው ቡሩንዲ በጀመረው ጨዋታ ኤርትራን 3 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።
በዛሬው ጨዋታ ደግሞ ከ ኢትዽያ አቻው ጋር 1 ለ 1 በመለያየቱ በቀጥታ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል። ከየምድቡ አንድ ቡድንና ከሶስቱ ምድቦች የተሻለ ሁለተኛ ቡድን አንድ በሚያልፈበት የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ በሦስት ነጥብ በሁለተኝነት አጠናቃለች።
የነገው የምድብ ” ሀ” ጨዋታ ከተደረገ በኃላ ከምድቡ አንደኛ የሆኑ እና ከሦስቱ ምድቦቹ የተሻለ ሁለተኛ ወደቀጣዩ ዙር የሚልፍ ይሆናል። በምድብ ” ሐ” ኬንያ ማለፉ ይታወሳል። ከነገው ጨዋታ በኃላ ምናልባት የተሻለ ሁለተኛ ሆኖ ለማለፍ ኢትዮጵያ ዕድሉ ይኖራታል።