ዜናዎች

የሴካፋው ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ሳምንት ወደ ባህርዳር ያቀናል ! – 7 ተጨዋቾች ዛሬ ተቀንሰዋል – ተጨማሪም ጠርተዋል

የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር በኢትዮጵያ ሊጀመር ሳምንታት ቀርተውታል። ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ሻምፒዮና    ከሰኔ 26/2013 ተጀምሮ እስከ ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ ትገኛለች።
ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኑን በተመለከተ የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ካደረጉ በኃላ ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተው ቡድን ዛሬ የወዳጅነት ጨዋታ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር አድርጓል።
በቡድኑ ውስጥ በጉዳት እና በሃዋሳ በሚካሄደው የጥሎ ማለፍ ውድድር ለክለባቸው እንዲሄዱ የተቀነሱ እንዳሉ ሆነው ከዛሬ የወዳጅነት ጨዋታ በኃላም የፋሲል ከነማዎቹ
የመስመር አጥቂዎች ናትናኤል እና አለምብርሀን ፣ ወጣቱ የሀዲያ ሆሳዕና አጥቂ ደስታ ዋሚሾ ፣ የቅዱስ ጊዮርጊሱ የመሃል ተከላካይ አማኑኤል ተረፉ፣ ኢትዮ መድህን ግብ ጠባቂ ታምራት ዳኘ እና አርባምንጭ ከነማ የተከላካይ አማካይ ኤርሚያስ በላይ  እና መሐመድኑር ናስር ከቡድኑ ቀንሰው  አዲስ ተጨዋቾች መጥረታቸው ሲሰማ። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሻምፒዮናው እስኪጀምር ድረስ የተጨዋቾች ስብስቡ ውስጥ የሚቀንሱቸው እና ተጨማሪ የሚካቱቷቸው እንዳለ ተሰምቷል።
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሰለጥነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለባህርዳሩ የሴካፋ ሻምፒዮና የአዲስ አበባ ዝግጅቱን አጠናቆ በቀጣይ ሳምንት ወድድሩ ወደ ሚደረግባት ወደ ባህርዳር ያቀናል።