የ17ኛው ሳምንት የመጀመሪያው ጨዋታውን ያደረገው እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር በባዶ ለባዶ ተለያየው የሰበታ ከተማ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ባለመሸነፍ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ ሲሆን የሰበታ ከተማ ክለብ በዛሬውም ጨዋታ በርካታ የጎል ዕድሎችን አግኝተው ሆኖም ጨዋታው በአቻ ያል ጎል ተለያየትዋል ። አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
ብዙ የማግባት ዕድሎቹን ያለመጠቀማቸውን በተመለከተ አሰልጣኙ ሲመልሱ ?
” እንግዴ ከረጅም ጊዜ በኋላ የመጀመሪያ ጨዋታችን እንደመሆኑ መጠን ነውና የመክፈቻውን ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት ከነበረን ጉጉት የተነሳ ብዙ ኳሶችን አምክነናል። ይህ ደግሞ ዛሬ የመጀመሪያው ሳይሆን ከዚህ በፊትም እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግሮች አሉብን። 1/3ኛው የእነሱ የመከላከያ ስፍራ ውስጥ ስንገባ ትንሽ የመረጋጋት ሁኔታዎች ይቀሩናል እሱን ማስተካከል ይጠበቅብናል። በተረፈ ግን ለሁለታችንም ጥሩ ጨዋታ ነበር ማለት እችላለሁ።
በጨዋታው 21ኛ ደቂቃ አካባቢ ከዳዊት እስጢፋኖስ ጋር ስላወራው ረጅም ነገር ?
” በፈገግታ …ዳዊት ልምድ ያለው ተጫዋች ነው። እሱ የእኛ ተከላካዮች ኳስ እያስነካ የሚያስወጣልን እሱ ነው። ስለዚህ በተቻለ መጠን ኳስን ተቆጣጥረን እየተጫወትን እነሱ 1/3ኛው የመከላከል ክፍል ውስጥ ቶሎ እንግባ ነበር ስለው የነበረው። ይህንን ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ አስተካክለው ሰርተውታል። ።