ዜናዎች

የሃድያ ሆሳና ተጨዋቾች ለዛሬው ጨዋታ አሁንም ወደ ድሬ አልተጓዙም ! ➖ ቡድኑ ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል

የ18ኛው ሳምንት የዛሬውን የመጨረሻ ጨዋታ ከአዳማ ከነማ ጋር የሚያደርገው የሀድያ ሆሳዕና ቡድን ተጨዋቾች አሁንም ድረስ ድሬዳዋ አልመጓዛቸው ታውቋል።
የተጨዋቾቹ ይህንን ውሳኔ ላይ የደረሱት የሁለት ወር ደመወዝ እና የፊርማ ገንዘብ በባንካችን ውስጥ ካልገባ ወደ ድሬደዋ ከተማ አንጓዝም በሚል ውሳኔ የደረሱ ሲሆን ተጨዋቹ በውሳኒያቸው አሁንም ፀንተዋል።የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋቾች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት በወሰኑት ውሳኔም ቡድኑ ልምምድ ያላደረጉ ሲሆን የምሽቱን ጨዋታ ላይ አዳማ ከተማ ጋር የማድረጋቸው ነገር ከሰአታት በኋላ የሚታወቅ ይሆናል።
ከሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋቾች በደረሠን መረጃ ቡድኑ ውሳኔውን ምናልባትም በመቀየር ከምሳ በኋላ ሊጓዙ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።
በአንፃሩ የዛሬ ምሽት ጨዋታውን ሀዲያ ሆሳዕና ከአዳማ ከተማ ጋር የማያደርግ ከሆነ ሁለት ዓመት ዕገዳን ሊያስተናግዱ እንደሚችሉም መረጃዎች ይጠቁማሉ።