ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ዛሬ ወሳኝ ድል ነው :ይሆን ጎል በማስቆጠሬ በጣም ደስ ብሎኛል ” – ሙጂብ ቃሲም

ቤትኪንግ የኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ለዋንጫው ጉዞ ተጠባቂው የፋሲል ከነማ እና የኢትዮዽያ ቡና ጨዋታ በሙጂብ ብቸኛ ጎል በአፄዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል። የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቡድን መሪነትነቱን በ35 ነጥብ አስጠብቆ የዋንጫ ግስጋሴውን ቀጥሏል።የጎሎ መሪነቱን በ13 ጎሎች በሁለተኝነት የሚከተለው ሙጂብ ቃሲም ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፖርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።ከአራት ጨዋታ በኃላ ወደ ጎል የመመለስ ስሜቱን ሙጁብ ተጠይቆ በዚህ መልኩ ምላሹን ይጀምራል ” በ አራት ጨዋታዎችን ጎል አላስቆጠርኩም ነበረ ። ኳሷዊ የሆነ ነገር ነውና ዛሬ ወሳኝ ድል ነው። ይሆን ጎል በማስቆጠሬ በጣም ደስ ብሎኛል” በማለት መልሷልየሊጉን አስራሶስተኛ ጎል ከማስቆጠሩ አንፃር በቀጣይ በጎል ፉክክሩ ውስጥ ለመቀጠል ስለሚያስበው ሲናገር ” ኢንሽ ዓላህ ለዋንጫ ነው አስበን የተነሳነው ። በዛ በመሃል እኔም ጎል እዬስቆጠርኩ ነው። ከጎል አሰቆጣሪዎች መሃል አንዱ በመሆኔም በጣም ደስ ይለኛል። ከዚህ በⷛላም ለቡድኔ ውጤት ለማስገኘት እኔም የተሻለ ጎል አስቆጥራለሁ የሚል እምነት አለኝ” ብሏልቡድኑህ ቅ/ጊዮርጊስንም ኢትዮጵያ ቡናንም ከማሸነፉ ጎን ለጎን የዋንጫ ቡድን ነው የሚል መንፈስ ውስጣችሁ አለህ ለሚለው ጥያቄ ሙጂብ ሲመልስ ” አዎ…በጣም አለ። የተሸነፍነውም አንድ ጨዋታ ነው። ትላልቅ ቡድኖች የሚባሉትን ሁሉንም አሸንፈናል። ይህም የዋንጫ ቡድን የሚያስብለው ሙሉ አቋም ላይ ነው ያለው ብዬ አስባለሁ” በማለት ሙጂብ ቃሲም ከጨዋታው በኋላ ለሱፐር ስፖርት ተናግሯል።