ዜናዎች

ዓሊ ሱለይማን የሊጉን የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ይዞ ሰሞኑን ወደ Göteborgs Atlet ክለብ ያመራል!

May be an image of 3 people, people playing soccer, people playing football and text
👇
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የቀናት እድሜ የቀረው ሲሆን ዛሬ የ30ኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ መርሃግብር ላይ የሀዋሳ ከተማዉ ኤርትራዊው አጥቂ ዓሊ ሱለይማን በክለቡ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ ሁለት ጎሎች አስቆጥሮ ክለቡ ወላይታ ድቻን አሸንፏል. እሱም የውድድር ዓመቱን በ20 ጎሎች የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ አጠናቋል.
ኤርትራዊው አጥቂ ዓሊ ሱለይማን ከሲውድኑ Göteborgs Atlet ክለብ የመጫወት ዕድል በማግኘቱ ሰሞኑን ወደ ስዊድን የሚያቀና ሲሆን በዛሬው ጨዋታ የሽኝት መርሐግብር ተደርጎለታል.
May be an image of 1 person, playing soccer, playing football and text