ዜናዎች

ዋልያዎቹ የወዳጅነት ጨዋታ ነገ ከሱዳን አቻቸው ጋር ያደርጋሉ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ከመጀመሩ በፊት  አቋሙን ለመፈተሽ ነገ የመጀመሪያ  የወዳጅነት ጨዋታውን  ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊው  አቶ ባህሩ ጥላሁን ባለፈው ሳምንት ቡድኑ ከአዲስ አበባ ከመነሳቱ በፊት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ዋልያውቹ  በካሜሩን የዝግጅት ጊዜያቸው ሁለት ወይም ሶስት   የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ማቀዳቸውን መናገራቸው ይታወሳል።

በዚህ መሠረት ዋልያዎቹ ነገ ከሰዓት  ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ ሲገለፅ ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ካሜሩን የደረሰው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታው  ለአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት እንደሚረዳቸው ተናግረው  የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከሶስት ቀናት በኋላ ዚምባብዌን እንደሚገጥም ተዘግቧል።

 

የሱዳን ብሄራዊ ቡድን  በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ 4  ከግብፅ ፣ ናይጄሪያ እና ጊኒ ቢሳው ጋር መደልደሏ ይታወሳል ።