የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ከታገደ በኋላ ኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሀገር ውጭ ለማድረግ በመገደዱ፤ የኢ.እ.ፌ በአማራጭነት ኬንያ፣ዚምቧቤን እና ደቡብ አፍሪካን መርጧል።
ሶስቱም ሀገራት ይህንን ጨዋታ ለማስተናገድ ፈቃደኝነታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የዚምቧቤ ስታዲየም የዚምቧቤን እና የኢትዮጵያን ጨዋታ ብቻ እንዲያስተናግድ በገደብ የተፈቀደለት እንጂ ሌላ ጨዋታ ማካሄድ እንደማይችል ካፍ በማረጋገጡ፤ ኬንያ ፈቃደኝነቷን የገለጸች ቢሆንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ዚምቧቤ ለመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታው ማቅናቱ ስለማይቀር፤ በአንድ የአውሮፕላን ጉዞ እና መጠነኛ ወጪ ጨዋታውን በደቡብ አፍሪካ ለማድረግ ወስኗል። በመሆኑም ጨዋታው ፊፋ በሚያስቀምጠው ቀን በደቡብ አፍሪካ ኦርላዶ ስታዲየም ለማድረግ የኢ.እ.ፌ ከደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ተስማምቷል።
@EFF
@EFF