
የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንዴት እየሄደ ነው እየሄደ ያለው ?
“የዘንድሮው የውድድር ዓመት አጀማመሬ አሪፍ ነበር መሃል አካባቢ ትንሽ የመቀዛቀዝ ነበር ከጉዳት ጋር ነገር ግ አሁን ወደ ተክክለኛው አቋም እየመየመጣሁ ነው ብዬ አስባለሁ።”
ዛሬ ስላስቆጠረው ጎል ?
” ጎሏን ሳስቆጥራት ፊቴን እንዳዞር ብቻ ነበር የፈቀዱልኝ እኔም ፊቴን እንዳዞርኩ ነበር የመታዋት እግዚአብሔር ፈቅዶ ኳሱ ተሳክቶልኝ ወደ ጎል ገብቷል”
በአንድ ሊግ ውስጥ ከሶስተ ወንድሞች ጋር አብሮ ስለመጫወት : አንተነህ ጉግስ አብሮት ይጫወታል በዚህ ላይ ሃሳቡን ?
” እዎ ! ከወንድም ጋር ስትጫወት በጣም ነው ደስ የሚለው። ኳሶች ሲበላሽብህ ያበረታታሃል፣ ችግርህን ይነግርሃል። በጣም ነው ደስ የሚለው ከወንድም ጋር መጫወት “
የዘንድሮው የውድድር ዓመት እንደቤተሰብ እቅድ አላችሁ ?
” ወላይታ ድቻን ከፍ ማድረግ ነው ዘንድሮ የምንፈልገው፤ ያሳደገን ቡድንም ስለሆነ።
በፋሲል ከነማ ስለሚገኘው ወንድሙ ሽመክት
” አዚህ ደረጃ ለመድረሴ ሽመክት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። የእሱን ፈለግ ነው የምከተለው። እሱ ነው የሚያበረታታኝ። እሱ ሲጠነክር እጠነክራለሁ። አሁን እሱም አሪፍ ላይ ነው።
ዛሬ ያስቆጠርከውን ጎል ለሽመክት ይሁንልህ ?
” በፈገግታ አይ ….ጎሉ ለእናት እና አባቴ ይሁንልኝ “