ዜናዎች

ከግብፁ ክለብ ጋር የተለያየው ሄኖክ የግብፁ ክለብ ላይ ለፊፋ ክስ መስርቷል! ⭕️ሄኖክ በደቡብ አፍሪካው Cape Town Spurs እና በኢራቁ Al karkh ክለቦች ጋር አዲስ መረጃ

 

የመስመር ተከላካዩ ሄኖክ አዱኛ ለግብፅ ክለብ ሃራስ ኤል ሁዶድ ከሦስት ወራቶች በፊት የሁለት ዓመት ፊርማውን በማኖር ለስድስት አመታት ከቆየበት የፈረሰኞቹ ቤት ወደ ግብጹ ክለብ ቢያቀናም ነገሮች እንደታሰቡት ሳይሆን ሄኖክ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ ኢትዮጵያ መገኘቱን ትላንት መዘገባችን ይታወሳል::
ኢትዮኪክ ለእናንተ ለአንባቢያን በገባንላችሁ ቃል መሠረት ሄኖክን ከክለቡ መለያቱን ተከትሎ መረጃውን የበለጠ ለማጣራት እንደምንጥር በገባነው ቃል መሠረት ጉዳዮን የበለጠ ለማጣራት ችለናል::
የሄኖክ እና አቤል ያለው እንዲሁም የሌሎችም ተጨዋች በግብፅ ሊግ ፕሮፌሽናል ዕድል አግኝተው እንዲጫወቱ የተጨዋቾች ወኪል በመሆን የሚታወቀው አዛርያስ ተስፋጽዮን የሄኖክ አዱኛን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ምላሽ ሰጥቶናል::እንደ ወኪሉ አዛርያስ ተስፋጽዮን ገለፃ ከሆነ ሄኖክ ከክለቡ ጋር በነበረው ስምምነት መሠረት ክለቡ መከፈል የነበረበት ገንዘብ ባለመክፈሉ መለያየቱን ገልፆ ጉዳዮን በህግ ለመፍታት ለፊፋ ክስ መጀመራቸውን እና ሄኖክ ከክለቡ ጋር መለያየቱን ተናግሯል::
በዚህ መሠረት አሁን ላይ ሄኖክ አዱኛ በሀገር ቤት እንደሚገኝ ወኪሉ አዛርያስ ገልፆል :: በአንፃሩ ሄኖክ በሌሎች ክለቦች ተፈላጊ መሆኑን በመግለፅ በቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አሰልጣኝ Ernst Middendrop የሚሰለጥነው የደቡብ አፍሪካው Cape Town Spurs እና በኢራቅ የሊግ ደረጃ 17ኛ ላይ የሚገኘው Al karkh ክለቦችን ጨምሮ በሀገር ቤት ያሉ የተለያዩ ክለቦች እርሱን ለመውሰድ ፍላጎት ስለማሳየታቸውም አዛርያስ ለኢትዮኪክ ተናግሯል::
እንደ ወኪሉ አዛርያስ ገለፃ አሁን ላይ ተጨዋቹ ተጠቃሚ መሆን ስለበት ከክለቦቹ ጋር ድርድር መሆናቸውን እና የተሻለ ክፍያ የሚቀርበው ክለብ የሄኖክ ቀጣይ ማረፊያ ክለቡ ይሆናል ብሏል::

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *