ዜናዎች

#ከዋልያዎቹ ከ4 እስከ 5 ተጨዋቾች በአሜሪካ ሊግ የመጫወት ዕድል ሊያገኙ ነው!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ አሜሪካ ከተጓዘ አንድ ሳምንት አስቆጥሯል።በቆይታውም ሁለት የወዳጅነት  ጨዋታዎችን ማሸነፉ ይታወሳል። ዋልያዎቹ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከጉያና ብሔራዊ ቡድን ጋር አድርገው በሽመልስ ሁለት ጎሎች ካሸነፉ በኋላ በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለተኛውን የወዳጅነት ጨዋታቸውን በሴግራ ፊልድ ከላውደን ዩናይትድ ጋር አድርገው 4 ለ2 አሸንፈዋል።በጨዋታ ላይ ጎሎቹን ሱራፌል ፣ ሽመልስ ፣ አስቻለውነ እና ይሁን ሲያስቆጥሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡድኑን የተቀላቀለው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ግብ ጠባቂ ዳንኤል ንጉሴ ደግም ፍፁም ቅጣት ምት አድናል ።
በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው  የወዳጅነት ጨዋታ ከማድረጉ ባሻገር አዳዲስ እና ለብሔራዊ ቡድኑ እንዲሁም ለተጨዋቾቹ የሚጠቅሙ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰሙ ይገኛል ። ታማኝ ምንጮች ለኢትዮኪክ ባደረሱት መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአሜሪካ ዋናው ሜጀር ሊግ ተወዳዳሪ ከሆነው ከዲሲ ዩናይትድ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ የክለቡን ምላሽ እየተጠባብቁ ባለበት ሰአት   ዋልያዎቹ ላውደን ዮናይትድን 4 ለ 2 ዛሬ ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ የተለያዩ ተጨዋቾችን የሚመለምሉ (Scouts) መገኘታቸውን እና በዛሬው ጨዋታ ከ 4 – 5 የሚደርሱ ኢትዮጵያን ተጨዋቾች ላይ ፍላጎት ማሳየታቸውን  ለኢትዮኪክ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ይኸው መረጃ እንደሚያመለክተው በተለይም ከነበሩት ስካውተሮች መካከል ዛሬ የተሸነፈው የላውደን ዮናይትድ ዋናው. ቡድን የሆነውና በአሜሪካ ሜጀር ሊግ የተወዳደረ የሚገኘው የዲሲ ዮናይት  Scouts ከዋልያዎቹ  ስብስብ ውስጥ  ከ4 እስከ 5 ቁጥራቸው የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ላይ  ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ና  በቀጣይ ቀናት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ሊሰሙ  እንደሚችሉ ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

One thought on “#ከዋልያዎቹ ከ4 እስከ 5 ተጨዋቾች በአሜሪካ ሊግ የመጫወት ዕድል ሊያገኙ ነው!

Comments are closed.