በደረጃ ሰንጠረዡ በስድስተኛ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በ18ኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ከባህርዳር አቻነው በ2 ለ2 አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
በወልቂጤ በኩል ጎል ካስቆጠሩት እና ድንቅ ብቃት ላይ ከሚገኙ ተጨዋች አንዱ ወጣቱ ጫላ ተሺታ ለሁለተኛ ጊዜ የጨዋታው ምርጥ ተጨዋቾች ተብሏል።ጫላ ተሺታ ከጨዋታው በኋላ አጭር ቆይታ አድርጓል።
–-ስለጨዋታው ሲናገር…
” ጨዋታው ትንሸ ከበድ ይላል። እነሱ ከሽንፈት ነበር የመጡት እኛ ደግሞ አሸናፊ ነበረን ። ያም ሆኖ አንድ ነጥብ ውጤት ይዘን ወጥተናል።
— የተቃራኒ ቡድን ካስቆጠራቸው ጎሎች መቆጠር በኃላ የእነሱ ስሜት….
“ያው በእግር ኳስ ዘጠና ደቂቃ አልቆ ፊሽካ እስኪነፋ ድረስ ተስፋ አልቆረጥንም ተሳክቶልናል”
–– እሱ ስላስቆጠረው ጎል
” ያው ልምምድ ላይ የተሰራ ነገር ነው። ሌላ አዲስ ነገር አይደለም። ልምምድ ላይ የሰራነውን ነገር የተገበርነው”
—ባለፉት ጨዋታዎች ካስቆጠራቸው ጎሎች አንፃር በአሰልጣኝ ተመስገን የተሻለ ነፃነት ስለማግኘቱ
“ከሚባለው በላይ አዎ…..”
–ከዚህ በፊት የውጭ አገር የሙከራ ዕድል ስማኝቱ እና አሁን ከጉዳት መልስ ይህ ዕድል ስለማሰቡ.….
” ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ወደ እዛው እየገባው ነው ብዬ ነው የማስበው ”
–-ከወልቂጤ ጋር ምን እንደሚያስብ….
“ከወልቂጤ ከተማ ጋር ረጅም እና ስኬታማ መንገድን አስባለሁ”
— የዛሬውን ጎል ለማን ትሰጣለህ?
” ለወልቂጤ ደጋፊዎች እኛን ብለው ለመጡት ደጋፊዎች ይሁንልኝ ”