
ፈረሰኞቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥር ሰባት ጨዋታ አሸንፈው ፣ በአምስቱ አቻ እና በሶስቱ ተሸንፈው በ26 ነጥብና በ 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ መሆኑ ይታወቃል።
በመሆኑም የቡድኑ ወጥ ያልሆነ ውጤት የክለቡ ኃላፊዎችንና ደጋፊውን ማስቆጣቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካዊው የ34 አመቱን አሰልጣኝ እንዲሰናበቱ አድርገዋል።
በምትኩም በቅርቡ የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ያደረጉትን የቀድሞ ተጨዋች ከአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሾመዋል። ፈረሰኞቹ ቀሪውን የውድድር ዓመት ከአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ጋር ይጨርሳሉ የሚለው ነገር እስካሁን እርግኛው መረጃ አልታወቀም።አሰልጣኝ ደረጄ ተስፋዬ ደግሞ ወደ ተስፋ ቡድን እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል ። በተያያዘ ከቡድኑ ከዲሲፕሊን ቅጣት ጋር ከዋተናው ቡድን ታግዶ የነበረው የፈረሰኞቹ የቀድሞ ኮከቡ እና አንጋፋ አጥቂ ሳላዲን ሰይድ ልምምዱን አጠናክሮ ከዋናው ቡድን ጋር መቀጠሉ ታውቋል።

