ዜናዎች

“ከስምንት ዓመት በፊት የአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ፕሮጀክት ኦኜ ነበር በቴሌቪዥን ስመለከት የነበረው ዘንድሮ በተራዬ በዋልያዎቹ እገኛለሁ” ➖ሱሊማን ሀሚድ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዋናው የዋልያዎቹ ስብስብ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የተካተተው እና ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የመጨረሻው 90 ደቂቃዎች ፍልሚያ አቢጂያን የሚገኘው ወጣቱ የሀዲያ ሆሳዕና ተጨዋች ሱሊማን ሀሚድ አንዱ ነው። የዋልያዎቹ የአሁኑ የኃላ መሥመር ደጀን ሱሊማን ሀሚድ ከዛሬ ስምንት አመት በፊት ብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ የዋንጫን ከሶሰት አሰርት አመታት በኋላ ሲቀላቀል እሱ ያኔ የ15 አመት ታዳጊ እና በአሶሳ የእግር ኳስ አካዳሚ ተጨዋች ነበር። እናም ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ዋልያዎቹ ሲያልፋ አሶሳን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያ በደስታ ሲፈነጭ እሱም በአካዳሚው ከጓደኞቹ ጋር በጭፈራ ካቀለጡት አንዱ ነበር ። በወቅቱ ታዲያ ሱሊማን የዋልያዎቹን አጥቂ ሳልሀዲን ሰኢድን ከሚያደንቃቸው እና ለማየት ከሚመኛቸው ተጨዋቾች አንዱ ነበርም ። በኃላም የብሔራዊ ቡድን እና ሳላዲን ምኞቱ ሰመሮለት ዘንደሮ ። በዋልያዎቹ ስብስብ  ኮትዲቯር ይገኛል ።ቀሪውን ሱሊማን ሀሚድ በኢትዮኪክ ቆይታው  ይነግረናል። ታነቡት ዘንድ እንጋብዛለን ።
ኢትዮ ኪክ :- የማዳጋስካር ጨዋታን መለስ ብዬ ላስታውስህ እና ድሉን እና ደስታውን እንዴት ታስታውሳለህ ?
ሱሊማን :- የማዳጋስካር ጨዋታ እስከ ዛሬ ካደረጋቸው ጨዋታዎች ሁሉ የተለየ ነበር። ለእኔ እጅግ የተለየና መጨረሻ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ አንደኛው ወሳኝ ዓላማችን ሲሆን ማዳጋስካርን በሜዳችን ማሸነፉ ትልቅ ደስታ ነበረው ነበር።
ኢትዮ ኪክ :- የማክሰኞ ጨዋታን በምን መልኩ ኮትዲቯር  ለማሸነፍ እየተዘጋችሁ ነው ? የቡድናችሁ ጥንካሬ?
ሱሊማን :- አሁን ላይ ያለው የብሔራዊ ቡድኑ ስሜቱ እጅግ ደስ የሚለው እና ጠንካራ ነው። እንደ ቡድን በጣም ጥሩ ነገር አለን። ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ በጣም በጉጉት  እና በዝግጅት ውሰጥ  ያለ ቡድን ነው ። በአላህ ፍቃድ ሰርተን እናልፋለን እላለሁ።
ኢትዮ -ኪክ :- በአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የቀረበ ቡድን ውስጥ አንዱ  በመሆነህ እና  የታሪክ አካል በመሆንህ የሚሰማውን ስሜት ግለፅልኝ ?
ሱሊማን :- በጣም ልዪ ስሜት ነው የሚሰማኝ ። የዚህ ታሪክ ደግሞ አንዱ አካል በመሆኔ በጣም ነው የምኮራው። ምክንያቱም ለሀገሩ ሁሉም ሰው ታሪክ መሥራት ይፈልጋል : እናም እኔ በዚህ ቡድን በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ።
ኢትዮ – ኪክ :- ከታዲጊ ቡድን ቀጥሎ በዋናው በብሔራዊ ቡድን ዘንድሮ የመጀመሪያህ ነው ፣ ከታዳጊ ቡድን ጋር ስሜቱ ?
ሱሊማን :- ከዚህ በፊት ከ 17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተጫውቻለሁ። በዋናው ብሔራዊ ቡድን ግን ዘንድሮ የመጀመሪያዬ ነው ። ስሜቱ በርግጥ ተመሣሣይ ቢሆንም ይሄኛው ለየት ይላል ስሜት ነው ።
ኢትዮኪክ :- ወደ ኃላ መለስ ብዬ ልጠይቅህና : ከስምንት አመት በፊት ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያልፍ የት ነበርክ ?
ሱሊማን :- ኦኦኦዎ …. በጣም አስታውሳለሁ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ባለፈበት ጊዜ የተወለድኩበት ስፍራ በአሶሳ በፕሮጀክት ሰልጣኝ ነበርኩ ።  ከስምንት ዓመት በፊት የአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ በፕሮጀክት ሆኜ  በቴሌቪዥን ስመለከት የነበረው ዘንድሮ በተራዬ   ታሪክ ለመድገም አሁን  በዋልያዎቹ አቢጃን እገኛለሁ ። ያኔ ከ15 አመት በታች የፕሮጀክት ፣ አሁን ደግሞ ከስምንት አመት በኃላ በብሔራዊ ቡድን በጣም የሚገርም ምኞት ነው ተሳክቶልኛል ።
ኢትዮኪክ :- በቲቪ ነበር ጨዋታውን ያኔ ስታይ የነበረው ? ስለነበረው ሁኔታ አስታውሰህ ንገረኝ ?
ሱሊማን :- አዎ በዚያን ጊዜ በቲቪ መስኮት ነበር። በጣም ደስ የሚል ትውስታ ነበር ። እንደውም በጣም ትልቁ አጋጣሚ ተፈጥሯል።
ኢትዮኪክ :- ምን ዓይነት አጋጣሚ ?
ሱሊማን :- በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን በጣም የማደንቀውን ሳልሀዲን ሰኢድን ያኔ በቴሌቪዥን ነበር የማየው። ያሰብኩት ተሳክቶ ሳልሀዲን ሰኢድን  በአካል ማግኘቴ በብሔራዊ ቡድንም መገናኘቴ በጣም ደስታ ተሰምቶኝ ነበር።
ኢትዮኪክ :- ያኔ ለአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ምን አደረክ ? ዘንድሮስ ብለናልፍ ምንስ ታደርጋለህ?
ሱሊማን :- ያንጊዜ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ በቴሌቪዥን አየተን አገር ምድሩም ነበር የተደበላለቀው ። እኔም ከዛን መሀል በጣም ስጨፍርም የነበረው ነበርኩ።ዘንድሮም ብናልፍ ደግሞ በቴሌቪዥን ሳይሆን ደስታዬን ሜዳ ላይ እገልፃለው። ደስታዬ ወደር የሌለው ይሆናል።
ኢትዮ – ኪክ :- በቲሙ ውስጥ የቅርብ ጓደኛህ ማነው?
ሱሊማን :- በብሔራዊ ቡድን ሁሉም ጓደኞቼ ቢሆኑም የቅርብ ጓደኛዬ ረመዳን ነው።
ኢትዮኪክ :- ስለ አቢጃን ያላችሁበት ሁኔታ አየሩ ? ስለ እነሱ የሰማችሁት ነገር?
ሱሊማን :- :- አየሩ ሁሉም ነገር አሪፍ ነው። ስለ እነሱ የሰማሁት የተለየ አዲስ ነገር የለም።
ኢትዮ – ኪክ: – በአጭር ቃል የአፍሪካ ዋንጫ ታልፋላችሁ?
ሱሊማን :- አዎ ! ነገ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍበት ቀን ይሆናል።
ኢትዮ – ኪክ: – መልካም ዕድል
ሱሊማን :- አመሠግናለሁ ኢትዮ – ኪክ !

2 thoughts on ““ከስምንት ዓመት በፊት የአፍሪካ ዋንጫ ስናልፍ ፕሮጀክት ኦኜ ነበር በቴሌቪዥን ስመለከት የነበረው ዘንድሮ በተራዬ በዋልያዎቹ እገኛለሁ” ➖ሱሊማን ሀሚድ

Comments are closed.