ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ

” ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ዋንጫ እስከማንሳትና ውድድሩን በደስታ ለመጨረስ ነው የምፈልገው” -መድኃኔ ብርሃኔ

በቤትኪንግ የ16ኛ ሳምንት ሀዲያ ሆሳዕና ዛሬ ሲዳማ ቡናን 2 ለ0 አሸንፎ ወጥቷል። የጨዋታውን ጎሎች ቢስማርክ አፒያ እና መድኃኔ ብርሃኔ አስቆጥረዋል።በደረጃ ሰንጠረዡም ሀዲያ ሆሳዕና በ26 ነጥብ በአራተኝነት ይከታል።የሀዲያ ሆሳህናው መድሀኔ ብርሃኔ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል ።በቅድሚያ ከጎል ማስቆጠሩ ዕርቆ የመጀመሪያውን ጎሉን ስለማስቆጠሩ የተሰማውን ስሜት ለተጠየቀው ሲመልስ ” በጣም ነው ደስ ያለኝ። የመጀመሪያው ጎሌም ስለሆነ :እንዲሁም ቡድኔም ስላሸነፈ ደስ ብሎኛል” ብሏል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመጫወት የእግርኳስ ህይወቱን ከማሳለፉ አንፃር በሜዳ ውስጥ የትኛው ቦታ መጫወት ትመርጣለህ ለሚለው ጥያቄ ” አሰልጣኝ አድርግ ያለኝን ቦታ ማዴረግ ስላለብኝ ሁሉም ቦታ ይመቸኛል” ካለ በኃላ ከተጫወትክባቸው ቦታዎች ውጤታማ የሆንክበት የትኛው ነው ነበር ለሚለው ጥያቄ ” በመስመር ላይ በምጫወትበት ሰአት ጎልም ስለማገባ እሱ ላይ የተዋጣሁ ነኝ ብዬ አስባለሁ ” ሲል ምላሹን ሰጥቷል።ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር በውድድር አመቱ ምን ደረጃ መድረስ ትፈልጋለህ ለሚለው ” ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ዋንጫ እስከማንሳትና ውድድሩን በደስታ ለመጨረስ ነው የምፈልገው” ብሏልየቡድኑ የባህርዳር ቆይታቸውን በተመለከተም ለተጠየቀው መድኃኔ ሲመልስ ” የባህርዳር ቆይታችን ብዙም ባያስደስትም : ጥሩ ነገር ይዘን አልሄድንም በመጨረሻ ግን በአሸናፊነት መደምደማችን ጥሩ ነገር ነው” በሚል ምላሹን ከሰጠ በኃላ ያስቆጠራን ጎሏን ለማን ይሆን ለሚለው መድኃኔ በፈገግታ ተሞልቶ ” ለምወዳት እናቴ” ይሁንልኝ ብሏል።