Uncategorized

“እጄን ደረቴ ላይ ማድረጌ የጃኖ ምልክቱ ሲሆን የእጄ ሰላምታው ደግሞ የፋሲል ሰራዊቱ ነው : የጎሏ መታሰቢያነት ከቀናት በፊት በሞት ለተለየው ለዓያቴ ይሁንልኝ ” ያሬድ ባዬ ( ፋሲል ከነማ )

ከ14ኛው ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታዎች አንዱ የነበረውና ዛሬ የተደረገው የሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ሲሆን በጨዋታው የመጠናቀቂያና የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል የለወጠው ያሬድ ባዬ ከጨዋታው በኃላ ከኢትዮኪክ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።በቅድሚያ ለያሬድ ጎሏን በማስቆጠሩ የተሰማውን ደስታ እንደገልፅልን ለጠየቅነው ” በጣም ትልቅ የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ። ከጨዋታው ትልቅ ግምት መሠጠትና የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ካለው ከፍተኛ ስም ጨዋታው ተጠባቂም ነበር። እናም ይህን ጨዋታ አሸንፎ መውጣት ትልቅ የደስታ ስሜት አለው ” በማለት ያሬድ መልሷልበጨዋታው ላይ ጎል አስቆጥራለው ብለህ አስበህ ነበር ለሚለው ” ተጨዋች እንደመሆኔ መጠን አዎ አስባለሁ። ከዚህ በተጨማሪም ፍፁም ቅጣት ምት ደግሞ ስናገኝ እንደማገባው አውቂያለው”ብሏልየዘንድሮው የፋሲል ከነማ ዓለማው ምንድነው ለሚለው ያሬድ ሲመልስ ” ዓላማችን ዋንጫውን ማንሳት ነው። እሱን ደግሞ አናሳካዋለን ” ሲል መልሷል ከጎሎ መገኘት በኃላ የደስታ ስሜቱ የገለፅክበት መንገድ ምስጢሩ ምንድነው ለሚለው ያሬድ በፈገግታ ተሞልቶ ” እጄን ደረቴ ላይ ማድረጌ የክለባችንን የጃኖ ምልክቱ ለመግለፅ ሲሆን ሌላው በእጄ ሰላምታው ደግሞ የፋሲል ሰራዊቱን በማሰብ ነው” በማለት በፈገግታ ተሞልቶ ገልፆታልበመጨረሻም ኢትዮ ኪክ የጎሉን መታሰቢያ ለማን ይሁን ትላለህ ለሚለው ያሬድ ” የጎሉ መታሰቢያነት ከቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ለዓያቴ መታሰቢያ ይሁንልኝ” ብሏል የፋሲል ከነማው አመለ ሸጋ አምበል ያሬድ ባዬ