ዜናዎች

እስራኤል አቅንቶ የነበረው ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ትላንት ተመልሷል! – ሰኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል !

ወደ እስራኤል አቅንቶ የነበረው  የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ልዑካን ቡድን  እና ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከእስራኤል አቻቸው ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ እና አበሮ የመስራት ስምምነት አድርጎ  ትላንት ተመልሷል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በአቶ ኢሳያስ ጅራ እና በዋና ፀሀፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን የተመራው የልዑካን ቡድን ከእስራኤል እግር ኳስ ማህበር ጋር የተሳካ ጅምር አብሮ የመስራት ስምምነት እና የU-17 ብሔራዊ ቡድኑ ደግሞ የወዳጅነት ጨዋታን በማድረግ  ከ6 ቀናት ቆይታ በኋላ ትላንት ተመልሷል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለስድስት ቀናት በእስራኤል ያደረገውን ቆይታ  በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰኞ ሰኔ 21/2013ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ወሎ ሰፈር በሚገኘው የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ለመስጠት የመገናኛ ብዙሃን ጋብዟል።