ዜናዎች

#ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ የ2024 አፍሪካ ዋንጫን ከሚመሩ ዋና ዳኞች ዝርዝር ውስጥ አንዱ ሆነዋል!

Ethiopian referee Bamlak Tessema Weyesa

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ)  በ2024 በኮትዲቫር ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ  ላይ  ጨዋታዎችን የሚዳኙ የመሀል ዳኞችን፣ ረዳት ዳኞችን፣ የቪዲዮ ረዳት ዳኞችን (VARs)፣ ቴክኒካል ኢንስትራክተሮችን  ጨምሮ   የVAR ቴክኒሻኖች እንዲሁም የ IT ባለሙያዎችን የቅድመ  ዝግጅት ኮርስ  የሚወስዱ አጠቃላይ የ85 ባለሙያዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ካፍ ይፋ  ባደረገው  የባለሙያዎች ዝርዝር ውስጥ  ከ26 ሀገራት ከተመረጡ 32 ዋና ዳኞች ዝርዝር   ውስጥ ኢትዮጵያዊው አርቢትር ባምላክ ተሰማ  ከቀዳሚዎቹ አንዱ ሲሆን የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ግብፅ እና አልጄሪያ  ሶስት ሶስት በማስመረጥ ቀዳሚ የዳኞች  ቁጥር አስመርጠዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ሞሮኮ፣ ሞሪታኒያ እና ሞሪሸስ ፣ኬንያ፣ኮትዲቯር ር እና ደቡብ አፍሪካ እያንዳንዳቸው  ሁለት ሁለት ዳኞች  ሲኖራቸው በዝርዝሩ ውስጥ የተካተቱት ሌሎች ሀገራት ጋቦን፣ ጋና፣ ቤኒን፣ ኮንጎ፣ ሶማሊያ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት ናቸው። በረዳት ዳኞች መዝገብ ውስጥ ያካተቱ  ብዙም ያልታወቁት ኮሞሮስ፣ ጅቡቲ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ከሌሎች ሀገራት በዚሁ የሚሳተፉበት ሲሆን ናይጄሪያ ከዝርዝሩ ውስጥ የለችም።