ዜናዎች

ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ የኩዌትን ሊግ ለመዳኘት ዛሬ ወደ ስፍራው ያመራሉ

የኩዌት እግር ኳስ ማህበር ሰሞኑን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከዲሴምበር 2-13/2021 በKuwait STC premier league የሚደረጉ ጨዋታዎችን የVAR እና የሜዳ ውስጥ ዳኛ ሆነው ውድድሮችን እንዲመሩ በጠየቁት መሰረት፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄን የተቀበለ ሲሆን፤ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማም ዛሬ ማምሻውን ወደ ስፍራው እንደሚያመሩ እና የኢ.እ.ፌ የተሳካ ጊዜ እንዲኖራቸው ተመኝቷል