አፍሪካ ዜናዎች

#ኢትዮጵያ ቀጣይ ጨዋታውን ከሞሮኮ ጋር ታደርጋለች!

👇
የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከማሊ አቻው ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ግቦች እሙሽ ዳንኤል ( 2x ) ፣ ማዕድን ሳህሉ እና መሳይ ተመስገን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ በድምር ውጤት ማሊን 6 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ መጨረሻው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።
አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ለተከታታይ አመታት ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር ማብቃት ችለዋል።
ኢትዮጵያ በመጨረሻው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ሞሮኮን የምትገጥም ሲሆን በደርሶ መልስ ጨዋታ የምታሸንፍ ከሆነ በቀጥታ ለአለም ዋንጫ ውድድር የምታልፍ ይሆናል።
የመጨረሻውን ዙር መቀላቀል የቻሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ፣ ሞሮኮ ፣ ካሜሮን እና ቡሩንዲ መሆናቸው ታውቋል።
የ2024ቱን ከ 20ዓመት በታች ሴቶች አለም ዋንጫ ውድድር ኮሎምቢያ የምታዘጋጅ ይሆናል።
@ቲክቫ ስፖርት