ወጣት አትሌት ቢኒያም የአለም ከ20 አመት በታች ክብረወሰንን ሰበሯል !
ኢትዮጵያን በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ የሚወክሉ አትሌቶች መምረጫ በስፔን ነርጃ ምሽቱን በተካደው የ10,000 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል።
ውድድሩን ፎትዬን ተስፋይ በ29፡47.71 በቀዳሚነት ስታሸንፍ ,ፅጌ ገብረሰላማ በ29፡49.33 እና እጅጋየሁ ታዬ 29፡50.52 ሁለተኛ እና ሶስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው አጠናቀዋል።
በተመሣሣይ በወንዶች የ10,000 ሜትር ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ 26:31.01 አሸናፊ ሲሆን አትሌት በሪሁ አረጋዊ 26:31.13 እና ሰለሞን ባረጋ 26:34.93 በሆነ ውጤት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው ድንቅ ፉክክርን አሳይተዋል.
በውድድሩ ላይ የወደፊት የርቀቱ ተስፈኛ ወጣት አትሌት ቢኒያም መርሀይ በሚገርም የማሸንፍ ብቃት በ4ኛ ደረጃ ከመውጣቱ በተጨማሪ የአለም ከ20 አመት በታች ክብረወሰንን በድንቅ ብቃት እና ቁርጠኝነት ሰበሯል .
በወንዶች 800 ሜትር ሚኒማ ለማሟላት የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል.