አትሌቲክስ ዜናዎች

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሌጎስ ማራቶን በማሸንፍ ከፍተኛውን ሽልማት አግኝተዋል !

በምዕረብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ለስድስተኛ ዛሬ ረፋድ በተካሄደው እና DSTVን  ጨምሮ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አግኝቶ በነበረው ” Access Bank Lagos City Marathon 2021 ” የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን  ከፍተኛውን ሽልማት በማግኘት ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሴቶች የ 42 ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮዽያዊቷ መሰረት ዲንቃ በ2:28.53 አሸናፊ በመሆን 30,000 ዶላር ተሸላሚ ስትሆን ኬኒያዊቷ ችሊስታይን ጄፕቺር በሁለተኝነት 20,000 ዶላር እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ ደስታ ሙሉነህ በሶስተኛነት 15,000 ዶላር ተሸላሚ ሆናለች። የ6ኛውን የአክሰስ ባንክ ሌጎስ ሲቲ ማራቶን በወንዶች ምድብ ኬንያዊው አማኑኤል ናይቤይ የ 42 ኪ.ሜ ውድድርን ቀዳሚ ሆኖ ሲያሸንፍ ። ኢትዮጵያዊያኑ ኤሬሳ ገለታ እና ደምስ ለገሰ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋልል።በዚህ መሠረት አሸናፊው ኬኒያዊው ናይቤይ 30,000 ዶላር ሲሸለም ፣ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ያገኙት ኢትዮጵዊያኑ ኤሬሳ እና ደምስ በቅደም ተከተል 20,000 እና 15,000 ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል።
ለስድስተኛ ጊዜ ዘንድሮ የተካሄደውን ሌጎስ ማራቶን በአፍሪካ ትልቁ ወድድር ለማድረግ እና አለም አቀፍ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ አዘጋጆቹ ጥረታቸውን የቀጠሉ ሲሆን ዘንድሮ ያደረጉት ጥረት የተሳካም ሆኖ የቀጥታ ሽፋን አግኝቷል። በዘንድሮው የሌጎስ ሲቲ ማራቶን ከ 100,000 በላይ አትሌቶች የታሰቡ ቢሆንም በኮቪድ ምክንያት 300 አትሌቶች በውድድሩ መሳተፋቸውን ታውቋል።