በዓለም የማራቶን ውድድሮች ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው አንዱ የሆነው ቺካጎ ማራቶን ለ45 ኛ ጊዜ ነገ ይካሄዳል። ከ6 ዋና ዋና አለም አቀፍ ማራቶኖች መካከል አንዱ የሆነውና በ5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የቺካጎ ማራቶን ላይ በሁለቱም ፆታ የዓለማችን ድንቅ አትሌቶች የሚወዳደሩ ሲሆን በውድድሩ ላይ ደግሞ ከ45 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችም ይሮጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በነገው ውድድር ከሚጠበቁ አትሌቶች በሴቶች አትሌት ገንዘቤ ዲባባ አንዷ ናት ። ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ለዚህ ውድድር ብላ ለረጅም ጊዜ ስትዘጋጅም የቆየች ሲሆን አሁንም በጥሩ ብቃት ላይ ትገኛለች።
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የነገው የችካጎ ማራቶን ለሁለተኛ ጊዜ ማራቶንን የምትሮጥም ይሆናል ። ገንዘቤ ከዚህ ቀደም በአምስተርዳም ማራቶን ተሳትፋ በ 2:18:05 በሆነ ሰአት ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ በተመሳሳይ ሲፋን በርቀቱ የመጀመሪያ ተሳትፎዋ 2:51:51 መጨረሷ ይታወሳል።
በዚህ የማራቶን ውድድር ላይ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሆላንዳዊቷ አትሌት ሴፋን ሀሰን በውድድሩ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች አንዷ ናት።
በተጨማሪም በነገው ማራቶን ከሚጠበቁ አትሌቶች ውስጥ ኬንያዊቷ ሩት ቼፕኔግቲች ስትሆን አትሌቷ በማራቶን 2:14:08 የተሻለ ሰአትም አላት ። በሴቶች ከገንዘቤ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያኑ አትሌት ትዕግስት ግርማ ፣ታዱ ተሾመ ፣ ሱቱሜ ከበደ እና አባበል የሻነህ የሚሳተፉ ይሆናል።
በወንዶቹ ፆታ በዓለም ሁለተኛው ፈጣኑ ሯጭ ኬንያዊው ኬልቪን ኪፕቱምም ለአሸናፊነት ቅድሚያ ግምቱን የተሰጠው ነው ። ከሱ ጎን ለጎን ከሁለት አመት በፊት ርቀቱን በቀዳሚነት በ 2:06:12 ያጠናቀቀው ኢትዮጵያዊው ድንቅ አትሌት ሰይፉ ቱራ ሌላኛው ተጠባቂ አትሌት ነው።
ከሰይፉ ቱራ በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያኑ አትሌት ዳዊት ወልዴ፣ ሁሰይዲን መሀመድ እና ሚልኬሳ መንገሻ በነገው የቺካጎ ማራቶን የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው።
ኢትዮ- ኪክ (ሊንኮቻችን)
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
#በቴሌግራም :-
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
ድረ ገጻችንን :-