ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ በአርባ ምንጭ ይፈፀማል!
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን፤ በቁርባን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።
ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት ሰጥቷል።
አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር።
ህልፈተ ሕይወቱ ዛሬ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም ንጋት ላይ የተሰማው የባሕር ዳር ከነማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው አለልኝ አዘነ በጉዳት ምክንያት ከክለቡ ስብስብ ጋር ያልነበረ ሲሆን በትውልድ ቦታው አርባ ምንጭ ሌሊቱን በድንገት ማረፉ ተሰምቷል።
ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ፣ መጋቢት 18 ቀን 2016 በአርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ከክለቡ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጋብቻውን በቁርባን ከፈፀመ 15 ቀናት ያልሞላው ግዙፉ ተጨዋች አለልኝ አዘነ ከአሟሟቱ ጋር በተያያዘ የተለያዪ መረጃዎች እየተሰሙ ነው።
”የአለልኝ የሞቱ መንስኤ ከቤተሰብ ጋር በትዳሩ ምክንያት አለመግባባት ነው ! ”
የካናል ፕሉሱ ጋዜጠኛ አብዱ ሞሀመድ
“…ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቹ ቤት አርባምንጭ ባለቤቱን ይዞ እንደሄደና ፡ ቤተሰቦቹ ትዳሩን እንዳልወደዱለትና ጭቅጭቅ እንደነበር፡ ከዛም ሞተሩን አሰነስቶ አዲስ ወደሚያሰራው የግል ቤቱ በመሄድ የኤልትሪክ ምሰሶ ላይ ራሱን አጠፋ ” ብሏል በዘገባው
ፈጣሪ ነፍስህን ይማረው !