ዜናዎች

#አቡበከር ናስር በኔዘርላንድ- አምስተርዳም  ይገኛል!-የመጀመሪያ የአውሮፓ ጨዋታውን ነገ ከቤልጂየሙ KAA Gent ክለብ ጋር ያደርጋል !

 

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  የፊት መስመር  ተጨዋቾች  አቡበከር ናስር  ከክለቡ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር   በኔዘርላንድ ይገኛል።

የደቡብ አፍሪካ  ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮ ሻምፒዮና የሆነው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ክለብ በ2023/24 የውድድር ዓመት  ከዲኤስቲቪ ፕሪሚየርሺፕ እና ከካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች በተጨማሪ በ  Nedbank Cup እና  MTN8  ውድድሮች የበላይ  ሆኖ ለመቅረብ በሀገር ውስጥ ሲያደርገው የነበረውን የቅድመ  ዝግጅት  በመጠናከር ከቀናት በፊት   ወደ አውሮፓ  ተጉዞ በኔዘርላንድ   ዝግጅቱን ቀጥሎታል።

ኢትዮዽያዊው አቡበከር ናስርም  ከቡድኑ ጋር በአውሮፖ የቅድመ ዝግጅት  ላይ  በኔዘርላንድ ይገኛል። የአቡበከር ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ በኔዘርላንድ  የሁለት ሳምንት  ቆይታው  አራት   የወዳጅነት ጨዋታዎች የሚያደርግ ይሆናል። ቡድኑ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን ነገ (አርብ)   ከቤልጂየም ፕሮ ሊግ  ቡድን  ከሆነው  KAA Gent ጋር የሚያደርጉ ሲሆን ቀሪዎቹ ጨዋታዎች ደግሞ  ከጠንካራው  የኔዘርላንድ ዋናው ሊግ ክለቦች ጋር የሚያደርግ   ይሆናል።

በዚህ መሠረት ማሜሎዲ ሰንዳውንስ. በቀጣይ ቀናት የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርጉባቸ ክለቦች እና ቀኑ  እንደሚከተለው ይሆናል።

👇

Mamelodi Sundowns vs KAA Gent (Belgium) – Friday, 21 July

Mamelodi Sundowns vs Go Ahead Eagles (Netherlands) – Sunday, 23 July

Mamelodi Sundowns vs Sparta Rotterdam (Netherlands) – Tuesday, 25 July

Mamelodi Sundowns vs NAC Breda (Netherlands) – Friday, 28 July