ትላንት ምሽት የሊዮን ሜስን ክለብ ላይ ድንቅ ጎሎችን በማስቆጠር ብቃቱን አሳይቷል!
የአሜሪካው MLS ሊግ የዓመቱ ውድድር እየተገባደደ ይገኛል። በዛው ልክ የሊጉ ፍልሚያው “ፕለይ ኦፍ” ውስጥ ከዘጠኙ ቡድኖች አንዱ ለመሆን የሚደረገው ትግልም ቀጥሏል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድንቅ ተጨዋች ማረን ኃይለሥላሴ የሚገኝበት ቺካጎ 12ተኛ ደረጃን ይዞ ትላንት ምሽት ከሊዮ ሜሲ ቡድን ኢንተር ሚያሚን ጋር ታላቅ ፍልሚያ አድርገው ነበር።
ይህን ጨዋታ በስታዲየሙ ተገኝቶ ለመታደምና የዓለማችን ድንቅ ተጨዋች ሊዮና ሜሲን ለማየት ከ65 ሺህ በላይ ተመልካች አስቀድሞ ትኬቱንም ቆርጦም ነበረ።
ይሁንና ሜሲ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት እንደማይሰለፈ የጨዋታው ዋዜማ ላይ ቢታወቅም ሁለቱም ቡድኖች ተጠባቂውን ጨዋታ ለማሸነፍ ታላቅ ፍልሚያ አደረጉ ።
ጨዋታው ተጀምሮ የመጀመርያው 45 ደቂቃ ሁለቱም ቡድኖች ጎል ለማስቆጠር እየተፈራረቁ ቢያጠቁም ሳይሳካ ቀረና በሁለተኛው አጋማሽ ላይ የትውልደ ኢትዮዽያዊው ክለብ ቺካጎ በጃርዳን ሻኪሪ አማካኝነት የመጀመርያውን ግብ አስቆጠረ ብዙም ሳይቆይ በራሳቸው ላይም ተቆጠረ።
ነገር ግን በ55ኛው ደቂቃ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ወጣት ማረን ኃይለሥላሴ ተቀይሮ ገባና የሜዳውን ድባብ በመለወጥ ታሪክ ሰራ።
በጨዋታው የቀጥታ ሽፋን የቴሌቪዢን ኮሜንታተሮቹ ስለዚሁ ድንቅ ታዳጊ ማረን እና ስለ ሻኪሪ በማውራት ላይ እንዳሉ ማረን ለቡድኑ ሁለተኛና ለራሱ የመጀመርያውን ጎልበ 62ኛው ደቂቃ አስቆጥረ እና ብዙም ሳይቆይ በ65ኛው ደቂቃም ለራሱ ሁለተኛውን ለቡድኑ ሦስተኛውን ጎል አስቆጥሮ በጋዜጠኞች ፣ አሰልጣኞች እንዲሁም በተመልካቹ ታዳጊው «Game changer» የሚለውን ስያሜም ማግኘት ችሏል።
በትላንት ምሽቱ ጨዋታ የማረን Chicago fire የሜሲን Inter Miamiን በትውልደ ኢትዮዽያዊው ማረን እና ሻኪሪ ጎሎች 4 ለ 1 አሸንፎ ወጥቷል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድንቅ ተጨዋች ማረን ኃይለሥላሴ እስካሁን ለ MLS ጨዋታዎች (በጥሎ ማለፍና ወዳጅነት ጨዋታዎች ሳይጨምር 6 ግቦችን በማስቆጠር የቡድኑ ከፍተኛ ግብ አግቢም እየመራም ይገኛል።