በስዊዘርላንድ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን አማካኝ ስፍራ ተጨዋች ያሳለፈው የ21 አመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ሃይለስላሴ ቡድኑ አሸንፎ እንዲወጣ ያሳቻሉትን ሁለት ወሳኝ ጎሎች አስቆጥሯል።
የአማካይ ስፍራው የወደፊት ኢንጂነር የሚል ስያሜን ያተረፈው ኢትዮጵያዊያዊው ታዳጊ ቅዱስ ኃይለ ሥላሴ በስዊዘርላንድ ዙሪክ ኤፍ ሲ ሁለተኛው ቡድን የሚጫወት ሲሆን ከሦስት ወራት በኃላ ከጉዳት መልስ በፈረንጆቹ የውድድር ዓመት የመጀመርያውን ጨዋታውን አድርጓል።
በስዊስ ከዋው ከሱፐር ሊግ ቀጥሎ ወደ ከፍተኛ ሊግ ለማለፍ በሚደረገው የፕሮሞሽን ሊግ ውድድር ላይ ክለቡ FC Zürich U21 ተጋጣሚውን Sc kriens በ 2 ለ 1 ውጤት ሲያሸንፍ በ60ኛው ደቂቃ ተቀይሮ የገባው ቅዱስ በ61ኛው ደቂቃ በመጀመርያ የነካትን ኳስ ወድ ጎልነት መቀየር በመቻሉ ቡድኑ 1 ለ 0 ለመምራት አስሎታል። ከሁለት ደቂቃ በኋላም ቅዱስ ከቀኝ በኩል የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔት በጭንቅላት ገጭቶ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሮ በመጨረሻም ቡድኑ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሽንፎ መውጣት ችሏል።
በተያያዘ መረጃ በስዊዘርላንድ ዋናው ሱፐር ሊግ ውድድር ለኤፍ ሲ ሉጋኖ ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር እና ድንቅ ብቃቱን በማሳየት አድናቆት ያተረፈው የቅዱስ ታላቅ ወንድም ማረን ሀይለስላሴ አዲሱን የ 2023 የውድድር ዓመት በአሜሪካ Major League Soccer (MLS) በማምራት ለቺካጎ ፋየር መቀላቀሉ ይታወሳል።
በተመሳሳይ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ቺካጎ ፋየር ከ ሚያሚ ጋር ባደረገው ጨዋታ ተሰልፎ ተጫውቷል።
የኢትዮ ኪክ (ሊንኮቻችን)
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
#በቴሌግራም :-
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_kick
🔛ድረ ገጻችንን :-
https://ethio-kickoff.com