ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ትልቅ ነገር አቅደናል፣ ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ለመውጣት ፣አይከብደንም ያንንም እናሳካዋለን ” ➖ወንድማገኝ ኃይሉ

በ20ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የምሽቱ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ ያደረጉት ጨዋታ የሃዋሳ አማካይ ወንድማገኝ ኃይሉ ባስቆጠረው ብቸኛ ጎል ጨዋታው ተጠናቋል።ከጨዋታው በኋላ ወንድማገኝ ከሱፐር ስፓርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።

ጎሉን ስታስቆጥር የነበረህ ስሜት ?
“በጣም ደስ ብሎኛል በጣም ደስ ያለኝ ደግሞ ማሸነፊያ ጎል ሆኖ ጨዋታው ካለቀ በኃላ ውጤቱን ስናይ በጣም ነው ደስ ያለኝ አግብቼ ማሸነፋችን”
ጉሉን ያስቆጠረበት መንገድ ?
” መጀመሪያ ኳሱን ለመስጠት ነበር ያሰብኩት ነገር ሳይ ተጨዋች መጣብኝ እሱን አልፌ ነበር ያገባሁት እና ተጠቅሜዋለው ያንን ክፍተት።”
በእንቅስቃሴ ላይ ከፊት ላይ ያሉት የሃዋሳ ከተማ አጥቂዎች ጥምረታቸው ጥሩ መሆን
“አሰልጣኛችን የሚሰጠንን ነገር አጥቂዎችም ፤ አማካይ ተጨዋቾችም በየቦታችን እንድንግባባ ተፅኖ ይደረጋል ያንንም ሜዳ ላይ አሳይተናል።”
ሃዋሳ ከተማ ዘንድሮ የሚያስቡት እስከምን ድረስ ነው ?
“ያሰብነው እስከዋንጫ ነበር ነገር ግን ሁኔታዎች አልተመቻቹም። እግርኳስ ላይ የሚያጋጥም ነው። አሁን ደግሞ ትልቅ ነገር አቅደናል። ቢያንስ ከአንደኛ አስከ ሦስተኛ ለመውጣት አይከብደንም፤ እናም ያንንም ነገር እናሳካዋለን  ፣ እስከ ሃዋሳው እስከ ፍፃሜ ድረስ ማለት ነው።”
ጎሉን ለማን መታሰቢያ ይሁን
 ለራሴና ለሰፈር ልጆች (በፈገግታ)”
Wondmagegn Hailu scores the winning goal for Hawassa Ketema
Hawassa Ketema