በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 14 ዓመታት በ7 ቁጥር መለያው በአጥቂው ቦታ ተወዳጁ ተጨዋች የነበረው ሳልሀዲን ሰኢድ ከፈረሰኞቹ ሊለያይ መሆኑን ኢትዮኪክ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
ተወዳጁ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምበል ሳልሀዲን ሰኢድ በ1999 ዓ.ም ልክ እንዳሁኑ በክረምት የዝውውር ወቅት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድንን የተቀላቀለው። በቅዱስ ጊዮርጊስ እያለ ለሶስት ዓመታት በግብፅ ሊግ የመጫወቱ ዕድል አግኝቷል። በኃላም ተመልሶ ፈረሰኞቹን ተቀላቅሎ ረጅም ዓመት ተጫውቷል ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታሪኩ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ዳግም እንዲመለስ ካስቻሉ ተጨዋቾች አንዱ የነበረው ሳልሃዲን ሰይድ ባለፉትን የውድድር ዓመታት በጉዳትና በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ በጨዋታዎች ሳይሰለፍ መቅረቱ ይታወሳል።
በተለይም አሰልጣኝ ማሂር ዴቪስ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ በነበሩ ሰዓት ሳልሀዲን ከቡድኑ ከዲሲፕሊን ቅጣት ጋር ከዋናው ቡድን ታግዶ እንደነበር አይዘነጋም ።
በቅርቡ አዲስ የውጭ አሰልጣኝ ለመቅጠር ስምምነት ማድረጉን ያሳወቀው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ከመምጣታቸው በፊት ከአንጋፍውን ተጨዋች እና
ከተወዳጁ ሳልሀዲን ሰኢድ ጋር የሚለያይ መሆኑ ተተረጋግጧል ። አንደ በታማኝ ምንጮች መረጃ መሠረት የሳልሀዲን ሰኢድ ቀጣይ ማረፊያ ጅማ አባጅፋር እንደሆነም ታውቋል።