ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ላይ ቅሬታውን አቀረበ !

ኢትዮዽያዊው ኢንተርናሽናል – ባምላክ ተሰማ የመሩት  ጨዋታ

 

በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አልጀርስ ላይ የትላንት ምሽቱ የሞሮኮው ዊይዳድ ካዛብላንካ ከአልጄሪያው ሚሲ አልጀርስ ጋር በ1 ለ1 አቻ ውጤት በተጠናቀቀው ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩትን ኢትዮዽያዊው  ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማ እና ረዳቶቻቸው ላይ የሞሮኮው ዊይዳድ ካዛብላንካ የዳኝነት ቅሬታውን ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ልኳል ፡፡ .
 
የዊይዳድ ክለብ በትዊተር ገፁ እና ለመገናኛ ብዙሃን በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የትላንቱ ጨዋታ ላይ
የመሀል ዳኛው ባምላክ ተሰማ እና ረዳቶቻቸው ጉልበት የተቀላቀለበትን ጨዋታ ላይ የክለባቸው (የዊይዳድ ክለብ ) በተቃራኒ ቡድን ግልጽ የሆነ እና የቀይ ካርድ የሚያሰጡ ጥፋት ቢደርስባቸውም ዳኞቹ ምንም ውሳኔዎች አለመስጠታቸውን አውግዘዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በየዊዳድ ክለብ በዋነኛነት ካፍ ጉዳዮን እንዲያጣራ የጠየቀበት የውሳኔ ሂደት የተፈፀመው በ 35 ኛው ደቂቃ የዊይዳድ የአጥቂ አማካይ ዋሊድ ኤል ካርቲ ያስቆጠረው ጎል በዳኞቹ ከጨዋታ ውጪ ማለታቸው አግባብ ባለመሆኑ ከካፍ በቅሬታቸው ማቅረቸው እና ምላሽ እንዲሰጣቸው ለካፍ ደብዳቤ መጠየቃቸውን በጋዜጣዊ መግለጫ ተጠቁሟል።
 
በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የዋይዳድ ካዛብላንካና ሚሲ አልጀርስ ጨዋታ በአጠቃላይ 37 ጥፋት የተሰሩ ሲሆን ለሁለቱም ክለቦች ሁለት ሁለት ቢጫ ካርዶችን በጨዋታው ተመልክተዋል።

ደብዳቤው

👇