አፍሪካ ዜናዎች

ቡሩንዲ ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ ሻምፒዮና ለዋንጫ አለፈች !

በኢትዮዽያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የነበረው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና ለዋንጫ ፍፃሜ የሚጫወቱት ቡድኖች ታውቀዋል። በባህርዳር አለም እቀፍ ስታዲየም ዛሬ በተደረገው ሁለተኛው  ለዋንጫ ፍፃሜ  የማለፍ ጨዋታ የቡሩንዲ ከ23 ዓመት በታች ቡደን   ለፍፃሜ ያለፈ ሌላኛዋ ሀገር ሆኗል ። የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና ለዋንጫ በረፋድ ጨዋታ ታንዛኒያ ደቡብ ሱዳንን 1 ለ 0 አሸንፋ ለዋንጫ ማለፏ ይታወቃል።
በዚህ መሠረት የዋንጫ ጨዋታው የፊታችች ዓርብ ቡሩንዲ ከታንዛኒያ አቻቸው ጋር የሚያደርጉት ይሆናል።
ቡሩኔዲ የዛሬውን ጨዋታ ከኬንያ ጋር 0 ለዐ መለያየታቸውን ተከትሎ በተሰጠው የመለያ ምት 4 ለ 2 አሸንፋ ለዋንጫ ደርሳለች።