የቶኪዮ ኦሊምፒክ የኢትዮዽያዊያን የሚሳተፉበት ውድድር ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 27/2013 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ይደረጋል።በዚህ ርቀት በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ እንዲወክሉ የተመረጡ አትሌቶች ከ1ኛ – 4ኛ ወጥተው ባመጡት ፈጣን ሰአት እንደሆነ ይታወቃል።
በአንፃሩ በ5ሺህ ሜትር በተደጋጋሚ በአጨራረስ የሚታወቀውና በርቀቱ ስመጥር የሆነውን የዓለም ድንቅ አትሌት ሞህ ፋራን ጭምር ያሸነፈው ሙክታር እንድሪስ በሀገር ውስጥ በተባለው ፈጣን ሰአት ( ሚኒማ) በ5ኛነት በመሆኑን በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሳይመረጥ በመጨረሻ ሰአት ቶኪዮ እንዲመጣ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ወስኖ አትሌቱ ቶኪዮ ይገኛል።
ከቀናት በፊት በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ3ሺህ ሜትር መሰናክል ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቶ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያስደሰተው አትሌት ለሜቻ ግርማ ከኢትዮጵያ ወደ ቶኪዮ ያቀናው ልክ አሁን ሙክታር እንድሪስ እንሆነበት ሲሆን በፌደሬሽኑ እና ኦሎምፒክ ፌዴሬሽኑ ውዝግብ በመጨረዎቹ ደቂቃዎች በኦሎምፒክ ኮሚቴ ውሳኔ እንደነበር ይታወሳል። በኦሎምፒክ ኮሚቴው ደግሞ ይህንን ከአትሌቶቹ ወቅታዊ ብቃት ተነስተው ውሳኔ የሚያስተልፉት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እና ብርሃኔ አደሬ ናቸው።
አሁንም በዛሬው የ5ሺህ ወንዶች የማጣሪያ ውድድር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሙክታር እንዲሰለፍ ባለመፈለጉ ስሙ እስካሁኑ ደቂቃ ዝርዝር ላይ የለም። አትሌቱ መሠለፉ አጠራጣሪ ነው። በተመሣሣይ ከቀናት በፊት የወርቅ ሜዳሊያ በብቸኛነት ያስገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ እንዲወዳደር ተፈልጎ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ኦሎምፒክ ኮሚቴ መስማማት ባለመቻላቸው በአንደኛው አካል ፍላጎት አትሌት ጌትነት ዋለ እንዲሰለፍ ተደርጓል።
በአሳዛኙ የሰዎች የራስ ስሜታዊነት እና የእርስ በእርስ ጦርነት አገር ክብራን በገሀድ እየተነጠቀች ትገኛለች።