ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” በጨዋታች ላይ ስሜታዊ እሆናለው :ነገር ግን አሰልጣኜ እየቀየረኝ ነው” ወሰኑ ዓሊ

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ተጋጣሚውን ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 አሸንፎ ተጠናቋል።በጨዋታው ለባህርዳር ከተማ ወሰኑ ዓሊ የማሸነፊያነቷን ጎል አስቆጥሯል። ወሰኑ ከጨዋታው በኋላ ከሱፐርስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል። ከረጅም ጊዜ በኃላ ወደ ጎል በመምጣቱ የተሰማውን ስሜት በመግለፅ ወሰኑ ይጀመራል ” በጣም ደስ ይላል ። ምክንያቱም ቡድናችን በተደጋጋሚ ያገኛቸውን ዕድሎች ያለጠቀም ችግር ነበረብን : ዛሬ በተወሰነ መልኩ ለማስተካከል ሞክረናል እና ተሳክቶልናል ብዬ አስባለሁ “ሲል ወሰኑ ገልጿል። ጎሉን ካስቆጠርክ በኃላ ወደ አስልጣኛቹ መሄድህ ጫናዎችን ማሳያ ነው ለሚለው ጥያቄ ” አዎ። አሰልጣኛችን በጣም እየለፋ ነው። እኛ ደግሞ እሱ በሚጠብቀን መንገድ እየሄድን አይደለም። ያንን ነገር በተወሰኑ መልኩ ለማስተካከል ሞከርን ። ያንን ለመግለፅ ነው ካገባው በኃላ ወደ እሱ የሄድኩት። የእሱም ደስታ ነውና ከእኛ በላይ እሱ ነበር የሚደሰቸውና።በጨዋታዎች ላይ ስሜታዊ በመሆን ካርድችን ያየህበት ጊዜ ነበሩና በቀጣይ ጨዋታዎች ምን ዐይነት ወሰኑ መመልከት ይቻል ለሚለው ” እውነት ነው በጨዋታች ላይ በጣም ስሜታዊ እሆናለው ነገር ግን አሰልጣኜ እየቀየረኝ ነው። የተሻለ ነገር እንደማመጣ እርግጠኛ ነኝ” በሚል ምላሹን አስቀምጧል ” ብሏልክለብህ ባህርዳር ከተማ በሁለተኛው ዙር የትኛው ደረጃ ላይ ይጠበቃል ለሚለው ወሰኑ ሲመልስ ” በተቻለን ወደ ተፎካካሪው ደረጃ ላይ ለመድረስ በእውነት። ምናልባትም ተፎካካሪዎችን ልዪነቱን እያሸፈን ነውና ነገር ግን እናጠበዋልን” በማለት ሃሳቡን ሰጥቷል🔛