አትሌቲክስ

#በካናዳ ኦትዋ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል!

  From Abdu Muhammed

 

በዘንድሮው ኦትዋ ኢንተርናሽናል ማራቶን በወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሎቶች አሸንፈዋል። በወንዶች ወደፊት ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበት አትሌት ይሁኝልኝ አዳነ በ 2፡08፡22 በመግባት አንደኛ ሲሆን ገብረጻዲቅ አብርሃ በ 2፡09፡13 በሁለተኝነት ፣ አብዲ አሊ ገልቹ በ 2፡10፡38 ሶስተኛ አሸንፈዋል።
በሴቶቹ ቀዳሚ ሆና የገባችው ዋጋነሽ መካሻ ስትሆን  ካናዳዊቷ ኤልሞር 2ኛ  በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ጀርመናዊ የሆነችው ሜላት ቀጀታ ደግሞ ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች፡፡