የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በታዳጊዎች እግር ኳስ ስልጠና ከሚሰራው የጀርመኑ ስሪ ፖይንትስ (3 Points) ፕሮጀክት ጋር በጋራ ለመስራት በጥር ወር 2014 በይፋ የስምምነት ፊርማ መፈራረማቸው ይታወሳል። እናም ከወራቶች በፊት የጀርመኑ ስሪ ፖይንትስ ተቋም ይፋዊና ከስምምነቱ በኋላ ቀጥታ ወደ ሥራ ገብቶ ታዳጊዎችን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን – ካፍ የልህቀት ማዕከል በማሰልጠን ከፍተኛ የሆነ ስራን ላለፉት ስምንት ወራቶች የሰራ ሲሆን ይህ ተቋም እያከናከናቸው ያሉ ተግባራት እና የታዳጊዎች ሥልጠናው በሀገራችን አልፎ ለአውሮፖ ክለቦች የሚበቁ ተጨዋቾችን ለማፍራት ሲሆን የስራ ውጤቱ ለውደፊት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ከፍተኛ ተስፋ ሰጪ ስራ ነው ማለት ይቻላል።
የስሪ ፖይንትስ ፕሌየርስ (3points ) ፕሮጀክት መስራች እና ባለቤት እንደሚታወሰው የቀድሞው የጀርመን ወጣቶች ብሔራዊ ቡድን እና በጀርመን ቡንደስሊጋው ስኬታማ ተጨዋች በአሁኑ ሰዓት ለጀርመኑ ኤፍ.ሲ ኮለን የፊት መሥመር ተጫዋች በቅርቡም የሚሞሸረው የትውልደ ኢትዮዽያዊው ዴቪ ሴልኬ ወላጅ አባት አቶ ቴዎድሮስ ሳሙኤል እንዲሁም የአካዳሚው ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ተገኝተው ናቸው።
የ3 Points ትልቁ ራዕይ በ2024/2025 ለኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድኑ እና በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋች ማፍራት ነው ” በማለት አካዳሚው ዳይሬክተር የቀድሞው የጀርመን ወጣቶች ብሔራዊ ቡድን እና በቦንድስሊጋ የሚጫወተውን የልጅ ልጃቸውን በቅርቡ የሚሞሽሩት አቶ አቶ ሳሙኤል ተገኝተው ከኢትዮ ኪክ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአፅንዖት ገልፀውልናል።
የነበረንን ሙሉ ቆይታችንን እንሆ :-
ኢትዮኪክ :- ስሪ ፖይንትስ (3 Points) ላለፉት ወራቶች ቆይታችሁ?
አቶ ሳሙኤል:- እንደሚታወቀው 3 points ካምፓኒያችን በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተመዝግበን ፣ በህጋዊነት እንደ አንድ የውጭ ኢንቬስተር ሆነን ነው ሰራችንን የጀመረውን ። ፕሮጀክቱ ስራውን ከጀመረ ሦስት ዓመት ሲሆነው አካዳሚው ስራውን ወደ ተግባር ከጀመርን ስምንት ወራት ተቆጥረዋል።
ኢትዮኪክ :- በዚህ በስምነቱ ወራት የሰራችሁት ስራዎች ምን ነበሩ ?
አቶ ሳሙኤል :- መጀመሪያ የተጨዋቾች ምልመላ ነበር። የታደጋዎቹ ምርጫ ያደረግነው የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው አመት ሐምሌ ወር ካዘጋጀው አገር አቀፍ የታዳጊዎች ውድድር ላይ ነበር። በወቅቱ ታዳጊዎቹ ጦርነት ከሌላቸው ሁሉም ክልሎች የተሳፈቡት ወደ 150 የሚሆኑ ልጆች ነበሩ ። በተጨማሪም ከአዲስ አበባ ከናዝሬትም የመጡ ነበሩ እነሱም አይተን ካዛ በኃላ ነው ። የታዳጊዎቹን ብቃት አይተን 30 ተጨዋቾችን የመረጥነው። ማንንንም በወገን ወይም በዘር በሃይማኖት ለይተን ምንም ያደረግነው ነገር የለም ።
ነገር ግን ታለንታቸውን የመረጥነው በተለያዩ በአገር እና ከውጭም ሀገር በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት ነበር የመረጥው ነገር የለም። ያልተመረጡት ልጆች ታለነት የላቸውም ማለት አይደለም ግን ካለን ቦታ የተሻለ የሆኑትን የመረጥነው።
በኃላ ላለፉት ስምንት ወራቶች በነዚህ ታዳጊ ተጨዋቾች ላይ ትልቅ ስራ ነበር ያደረግነው። በተለይም የተጨዋቾችን የፊትነስ ስራዎች፣ ለ120 ደቂቃዎች የመጫወት ብቃት ፣ የስነልቦና እና ከዚሁ ጎን ለጎን የቀልም ትምህርቶችን ላይ የግል ትምህርት ቤት በማስተማር እንዲሁም በቋንቋ የእንግሊዝኛ ለወደፊት የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ እነዚህን እንዲያዳብሩና ሁሉንም አብሮ እያስኬድን እየሰራን ነው። በተለይ ተጨዋቾች ከተለያዩ ቦታዎች ሲመጡ የስነልቦና ችግር በአንዳንዶች ላይ ይታይ ነበር ። ‘አልችለም ሳይሆን እችላለሁ’ የሚል ተነሳሽነት እና ልጆቹን በስነልቦና የማሳመን ላይ ፣ ባህሪ የማስተካከል ስራዎች ከተለያዩ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ሰርተናል። አሁንም የሀገር እና የውጭ የስነልቦና ባለሙያዎች አሉን ።
ኢትዮኪክ :- በአጭር ወራቶች ያያችሁት ነገሮች አበረታች ነው ይላሉ?
አቶ ሳሙኤል :- አዎ። በጣም ትልቅ ሂደት ነው። ባለፉት ሁለት ዓመታት ይህን ስራ ለመጀመር ከልጄ ጋር ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ ከ20 ጊዜ በላይ ተመላልሰናል። አሁን የጀመርነው ስራ ለማሳካት በርካታ መሠረታዊ ስራዎች ሰርተናል። ባለፉት ወራቶች ያየነው ነገር በቅርቡ ያሰብነውን አበረታች ነው። ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር እስካሁን ያለን የሰራ ጥምረት አበረታች ነው። ይኸም ይቀጥላል ብዬ አምናለሁ። በሀገር አቀፍ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ስምምነታችን ለብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችን ማፍራት ነው ሲሆን በ2024/2025 ዓመታት ውስጥ ዓላማችን በአውሮፓ ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋች ማሳካት የሚለው ሲሆን ይህንንም እንችላለን ብዬ አምናለሁ።
ኢትዮኪክ :- ይኸን እንዴት ልታሳኩት ትችላላችሁ?
አቶ ሳሙኤል :- 3 Points አካዳሚ በዋናነት ታዳጊዎችን አጎልብቶ ወደ አውሮፓ ገበያ የማስገባት ሥራ ነው ። የኔ የልጅ ልጄ ዴቪድ በ14 ዓመቱ እና በ18 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ተጫዋች በመሆን በ8.5 ሚሊዮን ዪሮ እና ከዛም ከ20 ሚሊዮን ዪሮ በላይ መፈረም የቻለው። እኛ ፕላናችችን ከ3-5 አመት በሚል ነው ፕላናችን ፣ አሁን እያየን ያለነው አበረታች ነው። በትክክል በታዳጊዎች ላይ ለመስራት ስናስብ በትክክል ከተሰራ ስኬቱ እንደለ ስለምናውቅ ጭምር ነው። በዚ ኢንቨስትመንት ትልቁ እና ከባዱ ብዙ ወጪ አለው ። ይህን ሁሉ ታሳቢ በማድረግ እኛም ያወጣነውን ለማግኘት የምንሰራው። ከዚህ በላይ ግን እነዚህ ተጨዋቾች ሀብትነታቸው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ከገቢው በላይ ዓላማችን የኢትዮጵያን እግር ኳስ ማገዝም ነው።
ኢትዮኪክ :- ታዳጊዎቹን በምን መልኩ ነው ወደ አውሮፓ ክለቦች የምታሳኩት?
አቶ ሳሙኤል :- ይሄ የእኛ በቅርብ ጊዜ የምንተገብረው ነው። በአካዳሚያችን የሚጫወቱ ታዳጊ ተጨዋቾቻንን ወደ አውሮፓ አገራት ለማጫወት ከጀርመን ሀገር ክለብ ጋር የ3 ዓመት partnership ተፈራርመናል። ስለዚህ ቀጣይ ጉዞ የሚሆነው ይህንን መተግበር ነው። ከዚህ በተጨማሪም ልጄ አቶ ቴዎድሮስ ሳሙኤል የእግር ኳስ ኤጀንት አለው። ለእኛ ይሄ ከባድ አይደለም። በቅርቡ የምንተገብረው ነው። ለእኛ ከባዱ እዚህ ያሉ አንዳንድ ችግሮ ናቸው።
ኢትዮኪክ :- ምን ዓይነት ችግሮች ? መጥቀስ ይችላሉ?
አቶ ሳሙኤል :- እንግዲህ በዋነኝነት እኛ የራሳችን አካዳሚ የለንም ያንን ደግሞ መገንባት እንፈልጋለን ። የወደፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እያዘጋጀን ከመሆኑ አንፃር መንግሥት መሬት እንዲሰጠን እንጠይቃለን ። አሁን ያለነው ፌዴሬሽኑ በሰጠን በካፍ የልህቀት ማዕከል ነው። ታዳጊዎቹ ስልጠናቸውን እዛው እየወሰዱ የምግብ፣ የማረፊያ፣ መዝናኛ ቦታው እዚሁ ነው። ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት እንዲያስተካክልልን የምንፈልገው የስፖርት ዕቃዎች ላይ ዕጋዊ የሆነ የተቀመጠ ነገር የለም። ለስፖርት የሚያስፈልጉ እቃዎች ኳስ ፣ ጫማዎች ሌሎችንም ቁሳቁሶች ላይ ከፍተኛ ክፍያዎች እያወጣን ነው ይህን ችግር መንግስት ቢያስተካክል እላለሁ።
ኢትዮኪክ :- ታዳጊዎቹን የሚያሰለጥኑ የአሰልጣኞች እና ባለሙያዎች በተመለከተ ምን የሚነግሩኝ አለ?
አቶ ሳሙኤል :- ስልጠናውን እተሰጠ ያለው በሀገር እና ከውጭ በሚመጡ ባለሙያዎች ነው። በቅር ብ ቀንም ከጀርመን ቁጥራቸው 45 ባለሙያዎች ይመጣሉ። የባለሙያዎች የአውሮፓን የሆቴል እና ሌሎችም መሉ ወጪ የሚሸፈነው በእኛ ነው። ከዚህ ሌላ የልጅ ልጄን ጨምሮ ታዋቂ በጀርመን ሊግ የሚጫወቱ ተጨዋቾችን በመጋበዝ ለታዳጊዎቹ የስኬት ልማዳቸውን የሚያካፍሉበት ሂደቶችን እንፈጥራለን።
ኢትዮኪክ :- በመጨረሻ የሚጨምሩት ነገር ካለ ?
አቶ ሳሙኤል :- ማንኛውም ባለሀብቶች ከእኛ ጋር መስራት የሚፈልጉ በስፖንሰርሺፕ ሊሆን ይችላል እንዲሁም በተለያየ መልክ ከአካዳሚያችን ጋር አብሮ መስራት ለሚፈልጉ በራችን ክፍት ነው።
ኢትዮኪክ :- ጥያቄን ከማጠናቀቄ በፊት በቅርቡ የልጅ ልጆት ዳቪድ ይሞሸራል ለሰርጉ ቢነግሩኝ ?
አቶ ሳሙኤል :- አዎ ። በጀርመን ቦንድስ ሊጋ ታዋቂ እና ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው የልጅ ልጄ ከሁለት ሳምንት በኃላ ይሞሸራል። እኔ እዚህ ባለበኝ በብዙ ስራዎች ምክንያት መገኘት ባልችልም ባለቤቴ እና ልጄ ሰርጉን ያደምቁታል ።