አትሌቲክስ ዜናዎች

-በቶኪዮ አየር ማረፊያ ለስድስት ሰዓታት ታግዶ የነበረው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከኮቪድ ነፃ ሆነ !

ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ጨዋታ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፣  ኮሮና ምክንያት ከአየር ማረፊያ እንዳልወጣ ተዘግቦ ነበረ ፣ይሁንና አሁን
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ልዑካን ቡድን ከቶኪዮ አየር ማረፊያ ወጥቶ ወደ ተመደበለት ቦታ መግባቱን የቡድኑ መሪ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው  ገልጸዋል።
ነገ በሚጀመረው 32ኛው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ለመሳተፍ ወደ ጃፓን ያመራው የመጀመሪያ ዙር የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ልዑክ ትናንት ቶኪዮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደረስ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን አቀባበል እንደተረገላቸው ተገልጾ ነበር።
በአንፃሩ ሪፖርተር ጋዜጣ “ልዑኩ በተሳፈረበት አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ የሞዛምቢክና የናይጄሪያ ልዑካን አባላት የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው በምርመራ በመረጋገጡ ሁሉም ተሳፋሪ ከቶኪዮ አየር ማረፊያ እንዳይወጣ መደረጉን” ዛሬ ከሰዓታት በፊት ዘግቦ ነበር።የልዑኩ መሪ ዶክተር ሂሩት ካሳው 30 የሚሆኑ አባላት የያዘው ቡድን በጃፓን ሰዓት አቆጣጠር 2 ሰዓት ከ30 ቶኪዮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መድረሱን ለኢዜአ ገልጸዋል።
ቡድኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጓዘበት አውሮፕላን ውስጥ የሞዛምፒክና የናይጄሪያ ልዑካን በትራንዚት መሳፈራቸውን ተናግረዋል።በአየር ማረፊያው በተደረገው ምርመራ የናይጄሪያ ልዑክ አባል በኮሮናቫይረስ በመያዙ ሁሉም ተሳፋሪ ከአየር ማረፊያው እንዳይወጣ መደረጉን ገልጸዋል።በአውሮፕላኑ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ የደረገላቸው ሲሆን ናሙና ተወስዶ ውጤቱ እስኪመጣ ድረስ ስድስት ሰዓት መፍጀቱንና በዚህም ምክንያት በአየር ማረፊያው መቆየት ግድ ማለቱን ተናግረዋል።
ረጅም ጊዜ የፈጀው የምርመራ ውጤት ከመጣ በኋላ የኢትዮጵያ ልዑክ አባላት ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ በጃፓን ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 9 ሰዓት በኋላ ከአየር ማረፊያው ወጥቶ ወደ ተመደበላቸው ቦታ መግባታቸውን ጠቁመዋል።
መረጃው@ Ena.et