ዜናዎች

“በሬውን ከጥጃ የሚለው ፕሪንስፕል ተግባራዊ አድርገን ነው ሻምፒዮና እንዲሁም ወደ ቤትኪንግ የተመለስነው ” ➖አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር (ዊሀ)

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ለቀጣዩ ዓመት ወደ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግን በወጣቱ አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር (ዊሀ) ተመልሷል።ወጣቱ አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር ትውልድ እና ዕድገቱ ልደታ በተለምዶ “ቤሪሞ” ሜዳ በሚባለው አካባቢ ሲሆን የዘጠናዎቹ ኮከብ በፈጣን አጥቂነቱም ብዙዎች ያስታውሱታል።

በተለይም በብሔራዊ ቡድን ከታዳጊ እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን በ1990 ዓ.ም ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢያመራም በጊዜው በጉዳት ምክንያት የፈለገውን ያህል አገልግሎት ሳይሰጥ ከወራት ቆይታ በኃላ ከፈረሰኞቹ ጋር በመለያየት ብዙዎች በተጨዋቾችን ሊያዮት ሳይችሉ ቀርተዋል። ይሁንና አሁን በአሰልጣኝነት በስኬት ተመልሷል።
ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ታችኛው ሊግ ወርዶ የነበረው አዲስ አበባ ከተማ ክለብ በቀጣይ ዓመት በቤትኪንግ ይወዳደራል። አዲስ አበባን በሻምፒዮናት ይዞ ከተመለሰው አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር ጋር ኢትዮኪክ ጋር ቆይታ አድርጋለች እንሆ :-
ኢትዮኪክ :- ሻምፒዮና ሆናችኃል ደስታው እንዴት ይገለጻል?
አሰልጣኝ እስማኤል :- በጣም መግለጽ በማይችል ቃል…ተደስተናል ። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኮቪድ ጋር በተያያዘ እግር ኳሱን ማስጀመሩ ትልቁ ነገር እሱ ነው ። ምክንያቱም ረጅም ጊዜ የተቋረጠ ቡድን ስለነበር በውድድር መመለሱ ለተጫዋቾቹ ፣ለአሰልጣኞቹም በአጠቃላይ ለባለሙያዎች ጥሩ ነው። እኛ ሻምፓና ሆነን ምንም እንኳ ገና ቀሪ ስስት ጨዋታ ቢኖረንም ።
ኢትዮኪክ :- ለክባችሁ አመቱ እንዴት ነበር ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- በኢትዮዽያ ሱፐርሊግ ምድብ ‘ ለ’ ላይ ተመድበን ከ12 ቡድኖች ጋር እየተጫወትን ነበር። ሃዋሳ ላይም ነበር ወልዲያም ላይ ነበር ውድድሩ ። ሻምፒዮን መሆናችንን ያረጋገጥነው ወልዲያ ላይ ነበር።
በዚህ አጋጣሚ ለክለብ ቦርድ አመራር ለስራ አስኪያጆች፣ ለተጨዋቾቹ እና በአጠቃላይ ለቡድኑ አባላት እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ።
ኢትዮኪክ :- ሻምፒዮና መሆናችንን ቀድማችሁ ነበር ያረጋጣችሁት ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- የሚገርምሽ አንዳንዴ እግር ኳስ ተአምር የሚታይበት ነውና … በዚህ በሱፐር ሊጉ ደረጃ ሲታይ ቡናችን ከ19 ጨዋታ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የተሸነፈው። እንደገና ሶስት ጊዜ አቻ ወጥተናል። 15 ጨዋታ አሸንፈናል። እናም ይሄ እራሱ በጣም ድርብ ድል አድርገን የምናየው ነው።
ኢትዮኪክ :- ብዙ ጎል ያልተቆጠረበት ቡድን አዲስ አበባ ነው የግብ ጠባቂ ጠንካራ ጎን ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- በ13 ጨዋታ አንድ ጎል ነው የገባብን እስካሁን። እንደገና ከ13 ጨዋታ 10 ጨዋታ በተከታታይ አሸንፈናል። ሁሉም ተጨዋቾች ናቸው የተደሰቱት ። ይሄ ማለት ኮከብ ተጨዋች ፣ ኮከብ ግብ አግቢም እንዲሁም ኮከብ ግብ ጠባቂም ለማሰመርጥ እየጣር ነው። ከዛ አኳያ ሁላችንም ተደስተናል።
ኢትዮኪክ :- የቡድህ ጠንካራ ክፍል የቱ ነው ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- የቡድናችን ጠንካራ ክፍል ምንመሰለሽ አንድ መርኸ አለን ይህም ምንድነው ” ማጥቃት ጨዋታ ያሸንፋል መከላከል ዋንጫ ያስበላል” የሚል መርህ በብድናችን ውስጥ አለ ። በዛ መርኸ አንፃር ሲታይ ትክክል ሰርቷል። ምክንያቱም መከላከለም ላይ በጣም ጠንካራ ነን ፤ማጥቃት ኃይላችንም በጣም ጠንካራ ነው። በወልዲያ ላይ በተደረገው ሁለተኛ ዙር ትላንትና ዘጠኛ ጨዋታችን ነበረ። እና በ9 ጨዋታ 2 ጊዜ አቻ ወጣን ሌሎች ላይ 14 ጎሎች አግብተናል ፤ በዛው አንፃር አንድም ጎል አልገባብንም ። ይኸ የሚያሳየው መከላከሉም ላይ በጣም ጠንካራ ነን ማጥቃቱም ላይ በጣም ጠንካራ ነን። ስለዚሀ ማጥቃት ጨዋታ ያሸንፋል መከላከል ጨዋታ ያሸንፋል ” በሚለው ፕሪንስፕል እየተገብርን ነው ማለት ነው።
ኢትዮኪክ :- የምትፈልጋቸውን ተጨዋቾች ይዘኸ ነው ለውጤት የበቃኸው ማለት እንችላለን ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- ዋናው ምን መሰለሽ…
በቡድናችን ውስጥ አብዛኞቹ ታዳጊ ተጨዋቾች ናቸው። በብዛት ዕድሚያቸው 23 እና 24 ላይ ያሉ ልጆች ናቸው። ከቡድኑ ወደ 80% የሚወስዱት በታዳጊ የዕድሜ ክልል ያሉ ልጆች ናቸው። እነዚህ ልጆች የሚመራ ልምድ ያለው ተጨዋቾች ደግሞ ያስፈልጋል። ከዛ ውስጥ አንዱ አሁን ሳምሶን አሰፋ {ግብ ጠባቂው) በጣም በብሔራዊ ቡድን ልምድ ያለው በትላልቅ ክለብ በመጫወት ልምድ ያለው ነውና ታዳጊዎችን በመምራት ጨዋታውን በማቅለል ትልቁን ሚና ተጫውቷል። ሮቤል ግርማ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ጥሩ አስተዋጽኦ ያደረገ ልጅ ነው እሱም ተጨዋቾችን በማታገል በመታገል ጨዋታውን ሲያቀል የነበረ ልጅ ነው። ከድር አዮብ (አምበሉ) እሱም እንደዚሁ ታክቲካሊ በጣም ጎበዝ ልጅ ነው ። የስራ ድርሻውን አውቆ ሲሰራ የነበር ልምድ ያለው ተጨዋች ነው። ሌሎችንም ተጨዋቾች የስራ ድርሻውን አውቀው በመምራት በማስተባበር ትልቁን ሚና የተወጣ ልጅ ነው። በተመሳሳይ ፊት ላይም ተክሉ ተስፋዬ እሱም የፊት ፊት አውራሪውን በመምራትና ጎሎች በማግባት አስተዋጽኦ አድርጓል።
ኢትዮኪክ :- ስለዚህ ልምድ ያላቸውን ተጨዋቾች በዋና ቦታዎች አድርገህ ታዳጊዎችን በዙሪያቸው እንደማለት ነው ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- አዎ..ከወጣቶች ጋር ልምድ ያላቸውን ዋናዋና ቦታዎች በማድረግ ጨዋታዎችን በማቅለል ትልቁን ሚና ተጫውቷል። በሬውን ከጥጃ በሚለው ፕሪንስፕል ተግባራዊ አድርገን ሻምፒዮና እንዲሁም ወደ ቤትኪንግ የተመለስነው የሆነው (በፈገግታ)። ፕሪንስፕሉ በጣም ተሳክቶልናል። በጣም በጣም ከሚገባው በላይ ተሳክቶልናል
ኢትዮኪክ :- እናንተ በሬውን ከጥጃ በሚለው ፕሪንስፕል ተግባራዊ ከማድረጋችሁ ጋር መስተዳድሩ ስላዘጋጀላችሁ ሽልማቱ ምን የምትለው አለ ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- እኛ በሬውን ከጥጃ ምናልባት የሚታረሰው መሬት (በፈገግታ) በመስተዳድሩ በኩል ሻምፒዮና ከመሆናችን ጋር ተዳምሮ ታላቅ ሽልማት እንደተዘሁ ይነገራል … እንግዴ የነሱን ይሄ ነው ብዬ ማወቅ አልችልም ። ግን እኛ የራሳችንን ሥራ አገባደን ጨርሰናል። የሚመለከተው አካሎች ደግሞ የሚሰሩት ስራ ስለሆነ ብዙም መረጃው የለኝም። ግን ከፍተኛ ሽልማት እንደማጠብቀን ተስፋ አደርጋለሁ።
ኢትዮኪክ :- ቀጣይ አዲስ አበባ በቤትኪንግ ምን ለውጥ ያደርጋል ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- ቀጣይ እቅዳችን የስራ አመራር ቦርድ በአዲስ መልክ ይቋቋም እና ከእነሱ ጋር ተነጋግረን እዛ ጋር አቅጣጫ ተቀብለን ለመስራት እየተዘጋጀን ነው ያለነው በእኛ በኩል።
ኢትዮኪክ :- በመጨረሻ ለዚህ ውጤት መሣካት የተባሩህ ወይም የምትጨምረው መልዕክት ካለ ?
አሰልጣኝ እስማኤል :- በጣም ደስ ብሎኛል ነው የምለው። በዚህ አጋጣሚ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ ለከተማ አመራሮች ፣ ለስፖርት ኮሚሽኑ እና ኮሚሽነሮች እንኳን ደስ ያላችሁ የሚለውን መልዕክት ማስላፍ ነው። የምፈልገው። ካዛ በተረፈ እጅግ ለምወዳት ለባለቤቴ ከአጠገቤ ሆና ትልቁን ስራ ስትሰራ ለነበረችው ዛያዳ ሻሚል እንኳን ደስ ያለሽ ማለት እፈልጋለሁ። እንደገና ወደ አሰልጣነቱ እንደመጣ ላደረገኝ ያሬድ የማነ ለሚባል እጅግ ለማክብረው እና ወደ አሰልጣነት እንደመጣ ያደረገኝና በዚህ አጋጣሚ እንኳን ደስ ያለህ እለዋለው። አመሰግናለሁ ።