ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ሾመ !

ከደቡብ አፍሪካዊ አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡
አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን በቂ ልምድ ያካበቱ ሲሆኑ፣ በርካታ ድሎችንም አሳክተዋል፡፡ እ.ኤ.አበ2015 እና 2016 የኬንያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ያነሱ ከመሆናቸው በተጨማሪ በ2015 የኬንያ ሱፐር ካፕ ምርጥ ስምንት አሸናፊም ሆነዋል፡፡ እንዲሁም የእንግሊዝ ከ17አመት በታች ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የ20111 አውሮፓ ሻምፒዮን ሆነዋል።
የ ዩ.ኤፋ ፕሮፌሽናል ላይሰንስ ያላቸው አሰልጣኝ ፍራንክ፣ ካሳኳቸው ድሎች በተጨማሪ ዌስትብሮም፣ ሬንጀርስና ሚድልስቦሮው ጨምሮ ዛማሌክ፣ ኸርትስ ኦፍ ሆክና ጉርማሂያ ክለቦች በፊትነስ፣ በዋናና ምክትል አሰልጣኝነት አገልግለዋል ።ከዚህ በተጨማሪ አሰልጣኙ በ2011 የፊፋ ኮቺንግ ኢንስትራክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በተጨማሪም የዪ.ኤፋ ኢንስትራክተር በመሆን ሰርተዋል፡፡
አሰልጣኝ ፍራንክ በዛሬው እለት ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አንጋፋ መሆኑን በመግለፅ ክለቡ የሚፈልገውን ውጤት ለማምጣትም በርትተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
መረጃው  ክቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ