
ከጨዋታው መጀመር በፊት የነበረበት ከፍተኛ ጫና ይታይ እንደነበር?
“አዎ! የሚያሳስበው ቅያሪ ተጨዋቾች ከሌለህ ኢኮኖሚካል ሆነህ መጫወት ነው። ቢሆንም እንደ አሰልጣኝ ቅያሪ ተጨዋች ሳይኖር መጫወት ያስጨንቃል። ግን ሜዳ ላይ ያየነው በተቃራኒ ነው ፤ ይሄ አጋጣሚ የመጣው ዓለም ላይም ስለሆነ ያጋጥማል። እንደ አሰልጣኝ ግን ያስጨንቃል….
በሁለተኛው አጋማሽ በተለይም ከውሃ ዕረፍት በኃላ ቡድኑ ለውጥ ስለማሳየቱ?
” በእርግጥ አዎ…አንዳንድ እንደዚህ አይነት ጨዋታዎች ከባዶች ናቸው… ምክንያቱም ተጋጣሚ ቡድንን አሳንሰህ መጫወት ትንሽ ይከብዳል። እና በእረፍት ሰዓትም መሀል ላይም ትንሽ ነቃ እንዲሉ እና ራሳቸውን እየጠበቁ ዘጠና ደቂቃውን እንዲጨርሱ እንጂ ሌላ ብዙ የተለየ ነገር የለም:። ግን ትክክለኛ ኳስ እንዲጫወቱ ትኩረት ሰጥተው በቀጣይ ጨዋታም ስላለ ታሳቢ አድርጋችሁ ተጫወቱ ነው ያልኳቸው። ትክክለኛ ክለቡን የሚገልፅ ነገር እንዲያሳዮ ነበር ቢሆንሞ ግን ከሞላ ጎደል የተሻለ ነገር ነበር የነበረው። ከእነሱ አንፃር ሲታይ መጨመር ነበረባቸው ቢሆንም ግን ቆንጆ ነው “
