ዜናዎች

ሰበታ ከተማ በፊፋ ዕገደ ሊጣልበት መሆኑ ተሰማ!

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በሁለተኛው ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዥ በ11ኛ ደረጃ የሚገኘው የሰበታ ከተማ ቡድን ከውጭ አገር አስፈርሞት ነገር ግን ደሞዝ  ባልከፈለው  ተጨዋች ጋር በተያያዘ በፊፋ ጠንከር ያለ እገዳ ሊተላፍበት መሆኑ ከፌዴሬሽኑ አካባቢ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃው ከሆነ ሰበታ ከተማ በክለቡ ውስጥ አስፈርሞት የነበረና አሁን ላይ ከቡድኑ ጋር እንደሌለ በተነገረለት የውጭ ተጨዋች ከ5ሺ ዶላር በማይበልጥ ያልተከፈለ ደሞዝ ምክንያት ዕገዳ ሊጣልበት እንደሚችል ተሰምቷል።

የመረጃው ምንጮች ለኢትዮ ኪክ ባሳወቁት መሠረት ተጨዋቹ ጉዳዪን ለፊፋ ማሳወቁን የሰበታ ከተማ ኃላፊዎች በማዋቀቻቸው ጉዳዮ  ወደ ዕገዳ ከማምራቱ  በፊት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኩል  በቶሎ ለመጨረስ ጥድፊያ ላይ መሆናቸው ታውቋል