ዜናዎች

ሉሲዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን በሰፋ የጎል ልዩነት አሸነፉ !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ምሽቱን በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረገው የመጀመሪያው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ተጋጣሚውን 9 ለ 0 አሸንፏል።በዋና አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚሰለጡንት ሉሲዎቹከደቡብ ሱዳን ያደረጉት ጨዋታ ከእረፍት በፊት አምስት ጎሎች በማስቆጠር በተጋጣሚያቸው ላይ የበላይነቱን ይዘዋል።
ጎሎቹን በስምንተኛው ሴናፍ ዋቁማ ፣ወዲያው በደቂቃ ልዩነት ሎዛ አበራ ፣ በ18ኛው ደቂቃ ሎዛ አበራ የግሏ ሁለተኛውን የቡድኑን ሶስተኛ ጎል አስቆጥራ ከሁለት ደቂቃ በኃላ የደቡብ ሱዳናዋ ሞዴስቶ አሲንዞ አረኛውን ስታስቆጥር አረጋሽ የመጀመሪያው አጋማሽ ከመጠናቀቁ በፊት አምስተኛውን ጎል አስቆጥራለች።
በኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የበላይነት በነበረው ጨዋታ ከእረፍት መልስ አረጋሽ ካልሳ ከዮርዳኖስ የተቀበለችውን ኳስ ወደ ጎል በመለወጥ በግሏ ሁለተኛውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 6ኛውን ጎል አስቆጥራለች  .
ጨዋታው እየተካሄደ የአዲስ አበባ ስታዲየም መብራት በመጥፋቱ ጨዋታው  ለ18 ደቂቃ መቋረጥ በኋላ ቀጥሎ ሲካሄድ ሎዛ አበራ ከመብራት መጥፋት መልስ 3  ጎሎችን አስቆጥራ ጨዋታው በሉሲዎች 9 ለ 0 መሪነት በሉሲዎቹ ቢይዙም   በጨዋታውየአዲስ አበባ ስታዲየም መብራት  በተደጋጋሚ በመጥፋቱም   በ80ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታው እንዱቋረጥ ተደርጓል ።  ከጨዋታው በኋላ በተሰጠ ውሳኔም ቀሪዎቹን ደቂቃዎች ነገ ረፋድ ሁለቱ ቡድኖቹ እንካሄዱ ተወስኗል።።