Kirizestom Ntambi
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ለእኔ የጨዋታው ምርጥ ማወሊ ነው፤ ሶስት ነጥብ ይዘን እንድንወጣ የቻለውን በእሱ በውጤት ነውና ” ➖ክሪዚሰቶን ንታንቢ ( ሰበታ ከተማ )

የሰበታ ከተማ ስፖርት ክለብ በ19ኛው ሳምንት ከጅማ አባጅፋር ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 አሸንፋዋል። የሰበታ ከተማ ቡድን የዛሬውን ጨወታ በማሸነፉም የደረጃ መሻሻል አድርገው በ7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሰበታ ከተማ በኩል የአማካኝ ክፍሉ በዛሬው ጨዋታ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ክሪዚሰቶን ንታንቢ ሲሆን ቡድንም ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ አስችሏል።
የሰበታ ከተማው አማካይ ተጨዋች ክሪዚሰቶን ንታንቢ ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።
የዛሬ ውጤት ለእሱ የሚሰጠው በመናገር ይጀመራል
” ይህ ውጤት ለእኔ በጣም ትልቅ ነገር ነው። ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ነው ወደ ኢትዮጵያ ሊግ የተመለሠክቱ። ስለዚህ ከሁለት አመት ቆይታ በኋላ የመጀመሪያውን ጨዋታዬ ላይ በድል መጨረሳችን ትልቅ ትርጉም አለው ለእኔ። ከዚህ በተጨማሪም ደረጃችን ማሻሻል የቻልንበት ስለሆነ ትልቅ ትርጉም አለው።
በድንቅ ብቃቱ  የታከለበተና ስላቀበለው ኳስ አስመልክቶ በልምምድ ሜዳ ተመሣሣይ ልምምዶችን ስለማደረጉ ተጠይቆ ሲመልስ ?
” አዎ ! እንደ አማካይ ቦታ ተጨዋችነቴ የማቀበል ስራም ላይ ልምምድ አደርጋለሁ። ስለዚህ በየጨዋታዎቹ ላይ ቢያንስ አንድ ትክክል የሆነ ኳስ ማቀበል አለብኝ የሚለውን ትኩረት አደርጋለሁ። ዛሬ ጥሩ ያቀበልኩት ኳስ ሶስት ነጥብ አስገኝቶልናል ።
አንተ ያሻግርካቸውን ኳሶች በቀላሉ እና ጥቅም ላይ የሚያውልል ተጨዋች ማነው ?
” እንደኔ እንደኔ ማወሊ ነው። ምክንያቱም ፈጣንና ጠንካራ ተጨዋች በመሆኑ።
የዛሬው ጨዋታ ምርጥ ላንተ ?
“ለእኔ የጨዋታው ምርጥ ማወሊ ነው። ምክንያቱም ሶስት ነጥብ ይዘን እንድንወጣ ያስቻለውን በእሱ ውጤት ነውና ያገኘነው እሱ ምርጥ ነበር “