ዜናዎች

” ለአቡበከር ደቡብ አፍሪካ ቢመጣ ትልቁ ፈተና ባህሉና እንግሊዝኛ መናገር ችግር ይሆንበታል ፣ ጌታነህ የደረሰበትን ችግር እንደ ትምህርት መጠቀም አለበት”

የቀድሞ የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ማሂየር ዴቪድስ

 

ኢትዮጵያዊው ድንቅ ልጅ አቡበከር ናስር በቀጣዩ የውድድር ዘመን በደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየርሺፕ እንዲጫወት ለማድረግ ከሶስት ያላነሱ የደቡብ አፍሪካ ክለቦች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው የደቡብ አፍሪካዊ ኪክ ኦፍ ዶት ኮም ትላንት ዘግቧል። በ2013 የውድድር ዘመን በ 23 ጨዋታዎች 29 ግቦችን አስቆጥሮ የኢትዮጵያ የከፍተኛ የጎል ሪከሩዱን የሰበረው የ21 አመቱ አቡበከር ናስር ፈላጊዎች የበዙ ሲሆን ተጨዋቹ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ክለቦች የኢትዮጵያ ቡናን በር እያንኳንኩ ይገኛል ።
ኪክ ኦፍ ዶት ኮም ዘገባ የደቡብ አፍሪካዎቹ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ፣ ኬፕታውን ሲቲ እና ባሮካ ኤፍሲ ሲሆኑ ኢትዮጵያ ቡና ከተጨዋቹ ጋር ካለው የረጅም ጊዜ ውል አንፃር እየቀረቡ ያሉትን ዓለም አቀፍ የዝውውር ጥያቄዎች ክለቡ በጥሞና እያጤንም እንደሆነ እየተነገረ ነው። የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ አሰልጣኝ የነበሩት ደቡብ አፍሪካዊው ማሂየር ዴቪድስ በአቡበከር ወደ ደቡብ አፍሪካ የመዘዋወር ጉዳይ  አሰመልክትው ለደቡብ አፍሪካዊ ኪክ ኦፍ ዶት ኮም ጋር ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ማሂየር ንግግራችን ሲጀምሩ
” የአቡበከር ችሎታው መጠራጠር አይቻልም። በዘንድሮ የውድድር ዓመት በርካታ ጎሎች አስቆጥሯል። በተለይ በቅጣት ምት ክልል ውስጥ የተረጋጋ እና ጥሩ ተጨዋች ነው። እንቅስቃሴዎች በውጤት በመቋጨት ረገድ በጣም ጥሩ ነው” በማለት አሰልጣኝ ማሂየር ተናግረዋል።
አሰልጣኙ ስለ አቡበከር ናስር ሲቀጥሉ” አቡበከር በዋነኝነት በአጥቂ ስፍራ ለክለቡ በተመሳሳይ ለብሔራዊ ቡድንም በ4 -3-3 አጨዋወት በቀኝ ክነፍ በኩል የፊት መስመር ላይ በቀላሉ ጎል ማስቆጠር የተካነ አስደናቂ ተጫዋች ሲሆን የተለየ ብቃት አለው። እርግጥ ነው ደቡብ አፍሪካ የተለየ ሊግ ነውና እዚህ ፍፁም ከዛ የተለየ ሊሆንበት ይችላልና ሊጉን ለማላመድ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድበት ይችላል” ዴቪድስ ለድረ ገፁ ይናገራሉ አያይዘውም
“የኢትዮጵያ ክለቦች አጨዋወት ተመሣሣይ በአብዛኛው በጣም በትንሽ ክፍቶች እና የተቀራረበ አጨዋወት ነው ፣ እዚህ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ደግሞ የተለየ ነው ። ቡድኖች የተቃራኒን አጨዋወት በቀላሉ ይተነትናሉ ወይም ያነባሉ ። ሲለዚህ ክፍተቶችን ወይም ቦታዎቹን ይዘጋሉ። እናም ያንን በትክክል ያውቃሉ። እናም አቡበከር ትንሽ የተለየ ፈጠራ ወይም ችሎታ ያለው መሆን እዚህ ይጠበቅበታል ” ብለዋል
የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ አሰልጣኝ ደቡብ አፍሪካዊው ማሂየር ዴቪድስ በአቡበከር ጉዳይ በተመለከተ ሲቀጥሉ”
“ለእኔ ለአቡበከር ትልቁ ፈተና የሚሆንበት ባህሉና ቋንቋ ሲሆን ።በቀዳሚነት ቋንቋው ችግር ይሆነበታል። እንግሊዝኛ መናገር ይችል እንደሆነ አላውቅም ፡፡ ጌታነህ ከበደ የደረሰበትን ችግር እንደ ትምህርት መጠቀም አለበት። እንደሚታወቀው ጌታነህ በብሔራዊ ደረጃ ከከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ሪከርዱ የሱ ነበር ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲመጣ። ነገር ግን የኢትዮጵያን ታሪክ እንደታሰበው እዚህ አላደረገውም ፡፡ በርግጥ እግር ኳስ ፣ አይታውቅም ፣ አቡበከር ወደዚህ መጥቶ በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ ሃትሪክ ሰርቶ እዚም ሊሳካለት ይችል ይሆናል። ማን ያውቃል? “
ካሉ በኃላ በመጨረሻም በቅዱስ ጊዮርጊስ  ከኢትዮጵያ ቡና በነበሩው የደርቢ ጨዋታ የአቡበከርን ሀትሪክ አስታውሰው በፈገግታ ተሞልቶ ሲቀጥሉ” አቡበከር
እኮ በእኛ ላይ ሃትሪክ ሰርቷል [በፈገግታ] እኛ እሱ ባስቆጠረው ሶስት ጎሎች 3ለ2 ተሸንፈናል፣ እና አቡበከር አደገኛ ተጨዋች ነው ” በማለት ለኪክ ኦፍ ዶት ኮም ተናግረዋል