ዜናዎች

ለባህርዳሩ የሴካፋ ሻምፒዮና – ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ!

 
የምስራቅ እና መካከለኛው ሀገራት ከ23 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከሰኔ 26/2013 እስከ ሐምሌ 11/2013ዓ.ም በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል።በዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ምክትሎቹ የሚመራ ሲሆን ለ35 ተጫዋቾችም ጥሪ አድርጓል። ወደ አፍሪካ ዋንጫው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሲያልፍ የቡድኑ አባላት ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል እድሚያቸው በብሔራዊ ቡድኑ እንዲካተቱ የሚፈቅድላቸው 5 ተጫዋቾች ቡድኑ ልምምድ ከጀመረ ሰባት ቀናት በኋላ ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀሉ ታውቋል። ምርጫው ከ13ቱም የፕሪሚየር ሊግ እና ከ4 ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ተደርጓል።
ጥሪ የተደረገላቸው የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ሰኔ 04/2013 ከጠዋቱ 4 ሰዓት ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ በመገኘት ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
2. የልደት የምስክር ወረቀት ከጀርባው ማህተም የተደረገበት
3. ፓስፖርት ያላቸው ተጫዋቾች ፓስፖርት ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ በ3 የተለያዩ ጊዜያት በዋና አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ጋዜጣዊ መግለጫውም
1. ቡድኑ ሲሰበሰብ ምርጫውን እና ቀጣይ ዝግጅቱን በተመለከተ
2. በዝግጅት መሃል የሚመቻች ጋዜጣዊ መግለጫ
3. የሴካፋ ውድድር ከመጀመሩ በፊት
ጥሪውን ፌዴሬሽኑ የሚዲያ አካላት እንዲያውቁት የሚያደርግ ሲሆን፤ የብሔራዊ ቡድኑን ዝግጅት ብቻ ቪዲዮ እና ምስል የሚዲያ አካላት ፕሮግራም በማሲያዝ መውሰድ ይችላሉ።
የሚከተሉት ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
1 ፋሲል ገ/ሚካኤል – ሰበታ ከነማ ግብ ጠባቂ
2 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ –  ሰበታ ከነማ አማካይ
3 ዱሬሳ ሹቤሳ  – ሰበታ ከነማ የመስመር አጥቂ
4 ሀ/ሚካኤል አደፍርስ  –  ሰበታ ከነማ የግራ ተከላካይ
5 አብድልከሪም ወርቁ –  ወልቂጤ ከነማ አማካይ
6 ያሬድ ታደስ –  ወልቂጤ ከነማ አማካይ
7 ፍቅሩ ውዴሳ  –  ሲዳማ ቡና ግብጠባቂ
8 ብርሀኑ አሻሞ – ሲዳማ ቡና የተከላካይ አማካይ
9 አማኑኤል እንዳለ  – ሲዳማ ቡና የቀኝ ተከላካይ
10 ይገዙ ቦጋለ-  ሲዳማ ቡና አጥቂ
11 ኪሩቤል ሃይሉ –  ፋሲል ከነማ የተከላካይ አማካይ
12 ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ  – ፋሲል ከነማ የመስመር አጥቂ
13 አለምብርሀን ይግዛው –  ፋሲል ከነማ የመስመር አጥቂ
14 ሀይሌ ገብረተንሳይ ኢት/ቡና የቀኝ ተከላካይ
15 ሬድዋን ናስር – ኢት/ቡና የተከላካይ አማካኝ
16 ዊሊያም ሰለሞን-  ኢት/ቡና አማካኝ
17 መናፍ አወል – ባህርዳር ከነማ የመሃል ተከላካይ
18 ሰለሞን ውዴሳ-  ባህርዳር ከነማ የመሃል ተከላካይ
19 ብሩክ በየነ – ሀዋሳ ከነማ አጥቂ
20 ወንድማገኝ ሀይሉ-  ሃዋሳ ከነማ አማካኝ
21 መስፍን ታፈሰ – ሀዋሳ ከነማ አጥቂ
22 ቸርነት ጉግሳ – ወላይታ ዲቻ የመስመር አጥቂ
23 ስንታየሁ መንግስቱ  – ወላይታ ዲቻ አጥቂ
24 በረከት ወልዴ – ወላይታ ዲቻ አማካይ
25 አቡበከር ኑሪ – ጅማ አባ ጅፋር ግብጠባቂ
26 ቤካም አብደላ – ጅማ አባ ጅፋር የመስመር አጥቂ
27 አማኑኤል ተርፋ-  ቅ/ጊዮርጊስ የመሃል ተከላካይ
28 አብዲሳ ጀማል – አዳማ ከነማ የመስመር አጥቂ
29 ሙዲን ሙሳ – ድሬደዋ ከነማ የመስመር አጥቂ
30 ፀጋሰው ድማሙ – ሀዲያ ሆሳና ተከላካይ
31 ደስታ ዋሼሞ – ሀዲያ ሆሳና አጥቂ
32 ወልደአማኑኤል ጌቱ – መብራት ሀይል ተከላካይ
33 እያሱ ለገሰ – አዲስ አበባ የመሃል ተከላካይ
34 ኤርሚያስ በላይ – አርባምንጭ ከነማ የተከላካይ አማካይ
35 ታምራት ዳኘ-  ኢት/መድህን ግብ ጠባቂ
 – የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

3 thoughts on “ለባህርዳሩ የሴካፋ ሻምፒዮና – ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ!

Comments are closed.