ዜናዎች

ሄኖክ አዱኛ(አላባ) ከግብፁ ክለብ ጋር መለያየቱ ተሰምቷል?

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በፈረሰኞቹ ቤት ለስድስት አመታት ድንቅ ጊዜን ካሳለፈ በኃላ በዘንድሮው አመት ወደ ግብፅ ተጉዞ በግብፅ ሊግ ሃራስ ኤል ሁዶድ ክለብ ወራቶች የቆየው
የቀኝ መስመር ተከላካዮ ሄኖክ አዱኛ(አላባ) ከግብፅ በሚወጡ ዜናዎች  ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተሰምቷል:: የቀድሞው የሀላባ ከተማ , ድሬደዋ ከተማ, ጅማ አባጅፋር , ቅ/ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀኝ መስመር ተጨዋች በዘንድሮው አመት ወደ ግብፅ መጉዙ ይታወሳል:: በአንፃሩ የግብፅ ሊግ ቆይታው አሁን ካለው መረጃ አንጻር ብዙም የተሳካ እንዳልሆነ እና ተጨዋቹ ወደ ሀገሩ መመለሱ ተዘግቧል::
ኢትዮ ኪክም የጉዳዩን እውነተኛነት ለማጣራት ሄኖክን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ቢሳካም በጉዳዪ ዙሪያ ሄኖክ በተለያዩ ምክንያቶች ምላሹን በቀጣይ ቀናቶች እንደሚሰጥ ለማወቅ ችለናል::
No photo description available.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *